አሞጽ 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እኔ ጌታ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኛው የእስራኤል መንግሥት እመለከታለሁ፤ እርስዋንም ከምድር ገጽ አጠፋለሁ፤ ሆኖም የያዕቆብን ዘር ሙሉ በሙሉ አልደመስስም። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 “እነሆ፤ የጌታ እግዚአብሔር ዐይኖች፣ በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤ ከምድር ገጽ፣ ፈጽሜ አጠፋዋለሁ፤ የያዕቆብን ቤት ግን፣ ሙሉ በሙሉ አልደመስስም፤” ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 እነሆ፥ የጌታ የእግዚአብሔር ዐይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ፊት አጠፋዋለሁ፤ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፥” ይላል ጌታ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እነሆ የጌታ የእግዚአብሔር ዐይኖች በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤ ከምድርም ፊት አጠፋታለሁ፤ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፤ ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እነሆ፥ የጌታ የእግዚአብሔር ዓይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ፊት አጠፋታለሁ፥ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፥ ይላል እግዚአብሔር። 参见章节 |