Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ድኾችን ጨቊናችሁ፤ እህላቸውንም አስገብራችሁ፤ ከጥርብ ድንጋይ ቤቶች ሠርታችኋል፤ እናንተ ግን አትኖሩባቸውም፤ የሚያስደስት ወይን ተክላችኋል፤ ነገር ግን ከእርሱ የሚገኘውን የወይን ጠጅ እናንተ አትጠጡም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እናንተ ድኻውን ትረግጣላችሁ፤ እህል እንዲሰጣችሁም ታስገድዱታላችሁ፤ ስለዚህ በተጠረበ ድንጋይ ቤት ብትሠሩም፣ በውስጡ ግን አትኖሩም፤ ባማሩ የወይን ተክል ቦታዎች ወይን ብትተክሉም፣ የወይን ጠጁን ግን አትጠጡም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እናንተም ድሀውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና፥ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ድሃ​ው​ንም ደብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ልና፤ መማ​ለ​ጃ​ንም ከእ​ርሱ ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ያማሩ ቤቶ​ች​ንም መር​ጣ​ችሁ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ነገር ግን አት​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ ያማሩ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ችም ተክ​ላ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ወይ​ንን አት​ጠ​ጡም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ድሀውንም ደብድባችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፥ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም።

参见章节 复制




አሞጽ 5:11
30 交叉引用  

ይህም የሚሆነው ድኻን ስለ ጨቈነና ያልሠራውንም ቤት በግፍ ስለ ወሰደ ነው።


እነሆ በፍሬያማው የእርሻ ቦታ አንድ እንኳ ደስተኛ የለም፤ በወይን ተክል ቦታዎች የእልልታና የዝማሬ ድምፅ አይሰማም፤ የወይን ጠጅ ለመጥመቅ የወይን ፍሬ የሚጨምቅ የለም፤ እግዚአብሔር የደስታ እልልታን ሁሉ እንዲቆም አድርጎአል።


ሀብትሽ ይማረካል፤ የንግድ ዕቃሽ ይዘረፋል፤ ቅጥርሽ ይፈርሳል፤ የተዋቡ ቤቶችሽ ይፈራርሳሉ፤ ድንጋዮችሽ፥ ሳንቃዎችሽና ፍርስራሹ ወደ ባሕር ይጣላሉ።


እናንተ በጎናችሁና በትከሻችሁ እየገፈተራችሁ ደካሞችን እንስሶች በቀንዳችሁ ወግታችሁ ወደ ሩቅ ቦታ ታባርሩአቸዋላችሁ።


ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ከዐውድማችሁ እህልን፥ ከመጭመቂያችሁም የወይን ጠጅን ከቶ አታገኙም፤ አዲስ የወይን ጠጅም አይገኝም።


የሚከተለውን አመጣባችኋለሁ፦ ታላቅ ድንጋጤን፥ ክሳትን፥ ዐይንን የሚያፈዝና ሰውነትን የሚያመነምን የንዳድ በሽታ አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁ የሚበሉት ስለ ሆነ ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ንጹሓንን በብር፥ ድኾችን በጫማ ይሸጡ ነበር።


ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በትቢያ ላይ ጥለው ራስ ራሳቸውን ይረግጣሉ፤ የተዋረዱ ምስኪኖችንም ገፍትረው ከመንገድ ያስወጣሉ፤ አባትና ልጅ ሁለቱም ከአንዲት ሴት ጋር ያመነዝራሉ፤ በዚህም ሥራቸው የተቀደሰውን ስሜን ያረክሳሉ።


የክረምቱንና የበጋውን ወራት የሚያሳልፉባቸውን ቤቶች ሁሉ እደመስሳለሁ፤ በዝሆን ጥርስ አጊጠው የተሠሩ ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ፤ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ይወድማሉ።”


በአሽዶድና በግብጽ በሚገኙ ምሽጎች ለሚኖሩ ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፦ “በሰማርያ ተራራ ላይ ተሰብሰቡ፤ እዚያ ውስጥም የሚፈጸመውን ግፍና ያለውን ሁከት ተመልከቱ።”


እንደ ባሳን ቅልብ ላሞች ሰውነታችሁን ያወፈራችሁ የሰማርያ ሴቶች ሆይ! ይህን ቃል አድምጡ! እናንተ ደካሞችን ታዋርዳላችሁ፤ ድኾችን ትጨቊናላችሁ፤ ባሎቻችሁ ሁልጊዜ የሚያሰክር መጠጥ እንዲያቀርቡላችሁ ትጠይቃላችሁ።


በእግዚአብሔር ትእዛዝ ታላላቅ ቤቶች ይፈርሳሉ፤ ታናናሽ ቤቶችም የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ።


ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።


እናንተ የችግረኞችን መብት የምትረግጡና ድኾችን ከአገር ለማጥፋት የምትፈልጉ ሁሉ! ይህን ስሙ!


ሕዝቤን እስራኤልን ወደ አገራቸው መልሼ አመጣለሁ፤ የፈረሱትን ከተሞች እንደገና ሠርተው በዚያ ይኖራሉ፤ ወይን ተክለው የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፤ ልዩ ልዩ ተክሎችን ተክለው ፍሬውን ይመገባሉ።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ሰማርያን በሜዳ ላይ እንደሚታይ የቤት ፍርስራሽ ክምር አደርጋለሁ፤ የወይን መትከያ ቦታ ትሆናለች፤ የከተማይቱንም ፍርስራሽ ድንጋይ ወደ ሸለቆ አፈሰዋለሁ፤ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።


የእርሻ ቦታ ሲፈልጉ የሌላውን ቀምተው ይወስዳሉ፤ ቤትም ሲፈልጉ ነጥቀው ይወስዳሉ፤ የሰውን መብት ረግጠው ሀብቱን ይዘርፋሉ።


እህል ትዘራላችሁ ሰብል ግን አትሰበስቡም፤ የወይራ ፍሬ ትጨምቃላችሁ፤ ነገር ግን በዘይቱ አትጠቀሙም፤ የወይን ፍሬ ትጨምቃላችሁ፤ የወይን ጠጅ ግን አትጠጡም።


ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ በዚያን ጊዜ ቤት ይሠራሉ፤ ነገር ግን አይኖሩበትም፤ ወይንም ይተክላሉ፤ ነገር ግን የወይኑን ጠጅ አይጠጡም።”


እነሆ ብዙ ዘርታችሁ ጥቂት ሰበሰባችሁ፤ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን አትጠግቡም፤ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን አትረኩም፤ ደራርባችሁ ትለብሳላችሁ፤ ነገር ግን አይሞቃችሁም፤ ሠርታችሁ የምታገኙት ደመወዝ ስለማይበረክትላችሁ፥ በቀዳዳ ኪስ ውስጥ የማኖር ያኽል ይሆናል።


ኤዶማውያን የተባሉ የዔሳው ተወላጆች “ከተሞቻችን ፈራርሰዋል፤ ነገር ግን መልሰን እንሠራቸዋለን” ቢሉ የሠራዊት አምላክ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ ይሠራሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ሕዝቡም ሁሉ አገሪቱን ‘የክፋት ምድር’ ኗሪዎቹንም ‘እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተቈጣው ሕዝብ’ ብለው ይጠሯቸዋል።”


“ልጃገረድ ለማግባት ታጫለህ፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይደፍራታል፤ ቤት ትሠራለህ፤ ነገር ግን አትኖርበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ነገር ግን በፍሬው አትጠቀምበትም።


እናንተ ግን ድኾችን ትንቃላችሁ፤ የሚጨቊኑአችሁና ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ ሀብታሞች አይደሉምን?


跟着我们:

广告


广告