አሞጽ 3:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ለጦርነት የሚያዘጋጅ መለከት በከተማ ውስጥ ሲነፋ በፍርሃት የማይንቀጠቀጥ ሕዝብ ይኖራልን? እግዚአብሔር ካልፈቀደ በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይመጣልን? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ጌታ ካላደረገው በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይሆናልን? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይደነግጡምን? ወይስ እግዚአብሔር ያላዘዘው ክፉ ነገር በከተማ ላይ ይመጣልን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን? 参见章节 |