Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 9:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 እርሱም እጁን ዘርግቶ ያዘና አስነሣት፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና ሌሎችንም አማኞች ጠርቶ ልጅቷን በሕይወት በፊታቸው አቀረባት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 እርሱም እጇን ይዞ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶቹንም ጠርቶ ከነሕይወቷ አስረከባቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እጁንም ለእርሷ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 እጁ​ንም ለእ​ር​ስዋ ሰጥቶ አስ​ነ​ሣት፤ ቅዱ​ሳ​ን​ንና ባል​ቴ​ቶ​ች​ንም ጠርቶ እር​ስ​ዋን አድኖ ሰጣ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 9:41
15 交叉引用  

እዚያም እንደ ደረሱ አባታቸውን “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በመላው ግብጽ ላይ አስተዳዳሪ ሆኖአል” አሉት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።


ኤልያስ ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ በመስጠት “ተመልከቺ፤ እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል!” አላት።


ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “አውጥተህ ውሰድ” አለው፤ ሰውየውም ጐንበስ ብሎ አነሣው።


ለሞት የተቃረቡትን ሰዎች ስለምረዳ መረቁኝ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ስለምረዳቸው በደስታ ይዘምሩ ነበር።


እግዚአብሔር መጻተኞችን ይጠብቃል፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆች ይረዳል፤ የክፉዎችን ዕቅድ ግን ያፈርሣል።


ኢየሱስም ወደ እርስዋ ቀረበና እጅዋን ይዞ አስነሣት፤ ትኲሳቱም ወዲያው ለቀቃት፤ ተነሥታም አስተናገደቻቸው።


ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በር አጠገብ ሲደርስ እነሆ፥ ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ከከተማይቱ ይወጡ ነበር፤ የሞተው ሰው ለእናቱ አንድ ነበር፤ እናቱም ባልዋ የሞተባት መበለት ነበረች፤ ከከተማይቱም ብዙ ሰዎች ተከትለዋት ነበር።


የሞተው ቀና ብሎ ተቀመጠና መነጋገር ጀመረ፤ ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለእናትዮዋ፥ “እነሆ፥ ልጅሽ፤” ብሎ ሰጣት፤


ሰዎቹም የዳነውን ወጣት ወደ ቤት ወሰዱት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ።


ቀኝ እጁንም ይዞ አስነሣው፤ ወዲያውኑ እግሩና ቊርጭምጭሚቱ በረታ።


ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአማኞች ቊጥር እየበዛ ሲሄድ የግሪክ ቋንቋ የሚናገሩ አይሁድ የይሁዳ አገር ተወላጆች በሆኑት አይሁድ ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ ያጒረመረሙትም በየቀኑ ይታደል በነበረው ርዳታ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ችላ ይሉባቸው ስለ ነበር ነው።


ሐናንያ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! ይህ ሰው በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ምእመናንህ ላይ ብዙ ክፉ ነገር ማድረጉን ከብዙዎች ሰምቻለሁ።


ጴጥሮስ በየአገሩ ሲዘዋወር ሳለ በልዳ ወደሚኖሩት ምእመናን ሄደ።


በእርግጥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች አክብራቸው።


በእርግጥ መበለት የሆነችና ብቻዋን የምትኖር፥ ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ አድርጋ ሌሊትና ቀን የእግዚአብሔርን ርዳታ በመለመን በጸሎት ጸንታ ትኖራለች።


跟着我们:

广告


广告