Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 8:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አንተ በመራራ ቅናት እንደ ተሞላህና የኃጢአት እስረኛ እንደ ሆንክ አያለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ምክንያቱም በመራራነት ተሞልተህ፣ በዐመፅ ሰንሰለት ተይዘህ አይሃለሁና።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በመራራ መርዝና በዐመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በመ​ራራ መርዝ ተመ​ር​ዘህ፥ በዐ​መፃ ማሰ​ሪያ ተተ​ብ​ት​በህ የም​ት​ኖር ሆነህ አይ​ሃ​ለ​ሁና።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና።”

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 8:23
18 交叉引用  

በሆዱ ውስጥ ግን ወደ መራራነት ይለወጣል፤ እንደ እባብ መርዝም ይሆንበታል።


እግዚአብሔር ሆይ! እኔ የአንተ ነኝ፤ የብላቴናይቱ አገልጋይህ ልጅ ነኝ፤ እስራቴን ፈተህልኛል። ከሞት ያዳንከኝ አንተ ነህ።


ኃጢአተኛን ሰው የገዛ ራሱ ክፋት ያጠምደዋል፤ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


ጌታ የሠራዊት አምላክ አገሪቱን በሞላ ለማጥፋት መወሰኑን ስለ ሰማሁ ማፌዝ ይቅርባችሁ፤ አለበለዚያ እስራታችሁ ይጠብቅባችኋል።


“እኔ የምደሰትበት ጾም የጭቈና ሰንሰለትና የፍትሕ መጓደል ቀንበር ታላሉ ዘንድ፥ ቀንበሩን ሰብራችሁ የተጨቈኑትን ነጻ ታወጡ ዘንድ አይደለምን?


ይሁዳ ሆይ! ይህ ሁሉ የደረሰብሽ በአካሄድሽና በክፉ ሥራሽ ምክንያት ነው፤ ይህም ሁሉ የመረረ መከራ የመጣብሽ በኃጢአትሽ ምክንያት ስለ ሆነ ወደ ሰውነትሽ ዘልቆ ልብሽን አቊስሎታል።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የማደርገውን ነገር ልንገራችሁ፤ ይህ ሕዝብ ምግቡ መራራ መጠጡም የተመረዘ ውሃ እንዲሆንበት አደርጋለሁ።


መከራዬንና ከርታታነቴን ማስታወስ እንደ እሬትና እንደ ሐሞት ሆነብኝ።


ከበባ አድርጎ ምርር ባለ ሐዘንና ችግር ውስጥ ከተተኝ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው፤


መራራነት፥ ንዴት፥ ቊጣ፥ ሁከት፥ ስድብና ማናቸውም ዐይነት ክፋት ሁሉ ከእናንተ ወዲያ ይራቅ።


እኛም ከዚህ በፊት ሞኞች፥ የማንታዘዝ እምቢተኞች፥ መንገዳችንን የሳትን ተላላዎች፥ ለልዩ ልዩ ፍትወትና ሥጋዊ ደስታ የተገዛን፥ በተንኰልና በምቀኝነት የምንኖር፥ የተጠላንና እርስ በርሳችንም የምንጣላ ነበርን።


ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።


“ነጻ ትወጣላችሁ” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል። ሰው ሲሸነፍ ላሸናፊው ባሪያ ሆኖ ስለሚገዛ እነርሱም ራሳቸው የኃጢአት ባሪያዎች ናቸው።


መላእክትን እንኳ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ እግዚአብሔር ሳይራራላቸው በጨለመ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆነው የፍርድን ቀን እንዲጠባበቁ ወደ ገሃነም ጣላቸው፤


跟着我们:

广告


广告