Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 7:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 “አባቶቻችን በበረሓ የምስክሩ ድንኳን ነበረቻቸው፤ ይህችንም ድንኳን እግዚአብሔር በነገረውና ባሳየው መሠረት የሠራት ሙሴ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 “እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው ንድፍና ባዘዘው መሠረት የተሠራችው የምስክር ድንኳን፣ ከአባቶቻችን ጋራ በምድረ በዳ ነበረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 “እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 “ሙሴን ተና​ግሮ እንደ አዘ​ዘው በአ​ሳ​የው ምሳሌ የሠ​ራት የም​ስ​ክር ድን​ኳን በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘንድ በም​ድረ በዳ ነበ​ረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 7:44
17 交叉引用  

ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን የቤተ መቅደሱን የዕቃ ግምጃ ቤቶቹን፥ በደርቡና በምድር ቤቱ የሚገኙትን ክፍሎችና ኃጢአት የሚሰረይበትን የቅድስተ ቅዱሳኑን አሠራር የሚገልጥ ዕቅድ ሰጠው።


ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት “ይህ ሁሉ እግዚአብሔር ራሱ በሥራ ላይ እንዳውለው በሰጠኝ መመሪያ መሠረት በጽሑፍ የሰጠኝ ዕቅድ ነው” አለ።


ስለዚህ ንጉሥ ኢዮአስ የሌዋውያኑን መሪ ዮዳሄን ጠርቶ፦ “የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ፥ እግዚአብሔር ለሚመለክበት ድንኳን አገልግሎት የሚሆን ግብር የእስራኤል ሕዝብ እንዲያዋጣ ያዘዘውን ሌዋውያኑ ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ሰብስበው ያመጡ ዘንድ ስለምን አላተጋሃቸውም?” አለ።


በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት ለመሥራት ጥንቃቄ አድርግ።


ድንኳኑን በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት ትከል።


በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት መሠዊያውን ከሳንቃዎች ሥራ፤ ውስጡም ባዶ ይሁን።


በሙሴ ትእዛዝ፥ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት የሌዋውያን ተግባር የሆነው የተቀደሰው ድንኳን ዕቃዎች ዝርዝር ቈጠራ እነዚህ ናቸው፦


ሕዝቡ ከግብጽ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ከምስክሩ ድንኳን በላይ የረበበው ደመና ተነሣ፤


አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት በምታገለግሉበት ጊዜ ከእናንተ ጋር በመሥራት ይረዱአችሁ ዘንድ፥ የሌዊ ነገድ የሆኑትን ወገኖችህን ውሰድ፤


የመገናኛው ድንኳን በተተከለበት ቀን ደመናው ድንኳኑን ሸፈነው፤ ከማታ ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ በድንኳኑ ላይ እንደ እሳት ያበራ ነበር፤


እርሱ የሚያገለግለው እውነተኛ ድንኳን በሆነችው መቅደስ ነው፤ ይህች ድንኳን የተተከለችው በሰው እጅ ሳይሆን በጌታ ነው።


እነዚህ ካህናት የሚያገለግሉበት ድንኳን በሰማይ ለሚገኘው ምሳሌና ጥላ ብቻ ነው፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኒቱን በሚሠራበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር “በተራራው ላይ እንደ ተገለጠልህ ዐይነት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ አድርግ” ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው።


ድል አድርገው ምድሪቱን ከያዙ በኋላ መላው የእስራኤል ሕዝብ በሴሎ ተሰብስበው እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳን ተከሉ።


ሕዝቡ ዮርዳኖስን ለመሻገር ድንኳኑን በነቀሉ ጊዜ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።


跟着我们:

广告


广告