Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 5:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ከዚህ በኋላ ሐዋርያቱን ወደ እነርሱ ጠርተው አስገረፉአቸው፤ የኢየሱስንም ስም በመጥራት እንዳይናገሩ አዘዙአቸውና ለቀቁአቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እነርሱም ምክሩን ተቀብለው ሐዋርያትን አስጠርተው አስገረፏቸው፤ ዳግመኛም በኢየሱስ ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ለቀቋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ሰሙትም፤ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፤ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እሺም አሰ​ኛ​ቸው፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ጠር​ተው ገረ​ፉ​አ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም በኢ​የ​ሱስ ስም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ገሥ​ጸው ተዉ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 5:40
13 交叉引用  

ደግ ሰው ለቤቱ እንስሳት ይራራል፤ የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።


ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን።


እናንተ ግን ናዝራውያንን የወይን ጠጅ በማጠጣት አሳታችሁ፤ ነቢያትንም ትንቢት እንዳይናገሩ ከለከላችሁ።


የእነርሱ ነቢያት “ትንቢት አትናገር፤ እንደዚህ ያለው ውርደት የማይደርስብን ስለ ሆነ ስለ ነዚህ ጉዳዮች ትንቢት አትናገር” ይሉኛል።


ሰዎች ወደ ፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራባቸውም ይገርፉአችኋል፤ ስለዚህ ከሰዎች ተጠንቀቁ።


ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነርሱም ያላግጡበታል፤ ይገርፉታል፤ ይሰቅሉታልም፤ ግን በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣል።”


ስለዚህ እነሆ፥ እኔ ነቢያትን፥ ጥበበኞችን፥ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹንም በምኲራባችሁ ትገርፋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዱአቸዋላችሁ


“እናንተም ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራቡም ይገርፉአችኋል፤ ምስክር እንድትሆኑኝ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ለፍርድ ትቆማላችሁ።


ወይኑ ባፈራ ጊዜ የወይኑ ተክል ባለቤት ከፍሬው ድርሻውን እንዲቀበልለት አንድ አገልጋይ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን አገልጋዩን ደብድበው፥ ባዶ እጁን ሰደዱት።


“የኢየሱስን ስም በመጥራት እንዳታስተምሩ በጥብቅ አዘናችሁ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ እናንተ ለዚያ ሰው ሞት እኛን ተጠያቂዎች ልታደርጉን ትፈልጋላችሁ።”


ሠላሳ ዘጠኝ፥ ሠላሳ ዘጠኝ ጅራፍ አምስት ጊዜ በአይሁድ ተገርፌአለሁ፤


跟着我们:

广告


广告