ሐዋርያት ሥራ 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ሁላችንም በመሬት ላይ ወድቀን ሳለ በአይሁድ ቋንቋ ‘ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? በሰይፍ ስለት ላይ ብትቆም ራስህን ትጐዳለህ’ የሚል ድምፅ ሰማሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ሁላችንም በምድር ላይ ወደቅን፤ እኔም በዕብራይስጥ ቋንቋ፣ ‘ሳውል፤ ሳውል፤ ለምን ታሳድደኛለህ? መውጊያውን ብትጋፋ ጕዳቱ በአንተ ይብሳል’ የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ ‘ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል፤’ የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ፦ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ? በሾለ ብረት ላይ መርገጥ ለአንተ ይብስሃል’ የሚለኝን ቃል ሰማሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ “ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል” የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ። 参见章节 |