Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 25:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እኔ ግን በሞት የሚያስቀጣው ምንም በደል አላገኘሁበትም፤ እርሱ ወደ ሮም ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ በማለቱ ወደዚያ ልልከው ወሰንኩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እኔም ለሞት የሚያበቃ አንዳች ነገር አለማድረጉን ተረዳሁ፤ ሆኖም ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ወደ ሮም ልልከው ወሰንሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፤ እርሱም ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቆረጥሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እኔ ግን ለሞት የሚ​ያ​ደ​ር​ሰው በደል እን​ዳ​ል​ሠራ እጅግ መር​ምሬ፥ እር​ሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ማለ​ትን ስለ​ወ​ደደ እን​ግ​ዲህ ልል​ከው ቈር​ጫ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፥ እርሱም ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቈረጥሁ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 25:25
11 交叉引用  

ከዚህ በኋላ መሪዎቹና ሕዝቡ፦ “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ስለ ሆነ ሞት አይገባውም” ሲሉ ለካህናቱና ለነቢያቱ ተናገሩ።


እንዲህም አላቸው፤ “ ‘ሕዝቡን ለሁከት ያነሣሣል’ ብላችሁ ይህን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት፤ እኔም እነሆ፥ በፊታችሁ መርምሬው ካቀረባችሁበት ክስ ሁሉ በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም።


በዚያን ጊዜ ጲላጦስ ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡም “በዚህ ሰው ምንም በደል አላገኘሁበትም” አለ።


ጲላጦስም “እውነት ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ። ከዚህ በኋላ ጲላጦስ እንደገና ወደ አይሁድ ወጣና እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤


የከሰሱትም ሕጋቸውን በሚመለከት ነገር መሆኑን ተረዳሁ፤ ነገር ግን ለሞት ወይም ለእስራት የሚያደርሰው ነገር የለም።


በዚህ ጊዜ ታላቅ ሁካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የሕግ መምህራንም ተነሡና “እኛ በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት ይሆናል፤ እኛ ምን እናውቃለን?” በማለት ተከራከሩ።


ይሁን እንጂ ስለ እርሱ ለጌታዬ የምጽፈው የተረጋገጠ ነገር የለኝም፤ ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈው ነገር እንዳገኝ ብዬ በፊታችሁ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! በፊትህ አቅርቤዋለሁ።


ከዚያም ወጥተው ሲሄዱ፥ “ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃው ምንም ነገር አላደረገም” ተባባሉ።


ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው።


ሮማውያን ከመረመሩኝ በኋላ በሞት የሚያስቀጣ ምክንያት ስላላገኙብኝ በነጻ ሊለቁኝ አስበው ነበር።


跟着我们:

广告


广告