Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 25:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ጳውሎስ ግን እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “እነሆ! እኔ ልፋረድበት በሚገባኝ በሮም ንጉሠ ነገሥት የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተም በደንብ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ያደረግኹት ምንም በደል የለም፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “አሁንም ቢሆን ፍትሕ ማግኘት በምችልበት፣ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ምንም በደል አልፈጸምሁም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጳውሎስ ግን “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሣር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጳው​ሎ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀ​ር​ባ​ለሁ፤ ፍር​ዴም በዚያ ሊታ​ይ​ልኝ ይገ​ባል፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ላይ የበ​ደ​ል​ሁት በደል እን​ደ​ሌ​ለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታው​ቃ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ጳውሎስ ግን፦ “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 25:10
12 交叉引用  

ይህን ያለበት ምክንያት ኢየሱስን በቅናት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ስለ ነበር ነው።


ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።


የከሰሱትም ሕጋቸውን በሚመለከት ነገር መሆኑን ተረዳሁ፤ ነገር ግን ለሞት ወይም ለእስራት የሚያደርሰው ነገር የለም።


ስለዚህ ከሳሾቹ ተሰብስበው ወደዚህ በመጡ ጊዜ ሳልዘገይ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ተቀመጥሁና ጳውሎስን በፊቴ እንዲያቀርቡት አዘዝኩ፤


እኔ ግን በሞት የሚያስቀጣው ምንም በደል አላገኘሁበትም፤ እርሱ ወደ ሮም ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ በማለቱ ወደዚያ ልልከው ወሰንኩ።


ፊስጦስ ከስምንት ወይም ከዐሥር ቀኖች ያልበለጠ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ካሳለፈ በኋላ ወደ ቂሳርያ ሄደ፤ እዚያ በደረሰ ጊዜ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠና ጳውሎስን እንዲያቀርቡት አዘዘ።


ከዚያም ወጥተው ሲሄዱ፥ “ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃው ምንም ነገር አላደረገም” ተባባሉ።


ሮማውያን ከመረመሩኝ በኋላ በሞት የሚያስቀጣ ምክንያት ስላላገኙብኝ በነጻ ሊለቁኝ አስበው ነበር።


ስውርና አሳፋሪ የሆነውን ነገር አስወግደናል፤ በተንኰልም አንሠራም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አንለውጥም፤ ይልቅስ እውነትን በይፋ እናሳያለን፤ ራሳችንንም ለሰው ሁሉ ኅሊና በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ እናደርጋለን።


跟着我们:

广告


广告