ሐዋርያት ሥራ 23:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ እኔ ግን የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅሁ ከወታደሮች ጋር ደርሼ አዳንኩት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 አይሁድ ይህን ሰው ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ ነገር ግን የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅሁ፣ ከወታደሮቼ ጋራ ደርሼ አተረፍሁት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ባሰቡ ጊዜ ከጭፍሮቹ ጋር ደርሼ አዳንሁት፤ ሮማዊ እንደሆነ አውቄ ነበርና። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ይህን ሰው አይሁድ ያዙት፤ ሊገድሉትም ፈለጉ፤ ከወታደሮችም ጋር ተከላከልሁለት፥ የሮም ሰው መሆኑንም ዐውቄ አዳንሁት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ባሰቡ ጊዜ ከጭፍሮቹ ጋር ደርሼ አዳንሁት፥ ሮማዊ እንደ ሆነ አውቄ ነበርና። 参见章节 |