Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 22:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እስከዚህ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ የጳውሎስን ንግግር ያዳምጡ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦ “እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከምድር ላይ ይወገድ! እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት መኖር አይገባውም!” እያሉ ጮኹ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሕዝቡም ይህን ቃል እስኪናገር ድረስ ሰሙት፤ ከዚህ በኋላ ግን ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ፣ “ይህስ ከምድር ገጽ ይወገድ! በሕይወት መኖር አይገባውም!” ብለው ጮኹበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከጳ​ው​ሎ​ስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕ​ይ​ወት ሊኖር አይ​ገ​ባ​ው​ምና እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ከም​ድር አስ​ወ​ግ​ደው” እያሉ ጮሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፥ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና አሉ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 22:22
6 交叉引用  

ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ “ይህን ሰው አስወግደው! በርባንን ግን ፍታልን!” እያሉ በአንድ ድምፅ ጮኹ።


እነርሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው። የካህናት አለቆችም “ከሮማው ንጉሠ ነገሥት በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም!” ሲሉ መለሱለት።


ሕዝቡም “ይገደል!” እያሉ በመጮኽ ይከተሉት ነበር።


እንዲህም አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ! አይሁድ ‘ይህ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት መኖር አይገባውም’ በማለት እየጮኹ በኢየሩሳሌምም፥ በዚህም እንዲፈረድበት የጠየቁኝ ይህ የምታዩት ሰው ነው።


አሕዛብ የሚድኑበትን ቃል እንዳንናገር እንኳ ይከለክሉናል፤ በዚህ ዐይነት ኃጢአትን በኃጢአት ላይ እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ ስለዚህ በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቊጣ መጥቶባቸዋል።


跟着我们:

广告


广告