ሐዋርያት ሥራ 11:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ያላንዳች ማመንታት ከእነርሱ ጋር እንድሄድም መንፈስ ቅዱስ ነገረኝ፤ እነዚህ ስድስት ወንድሞችም ከእኔ ጋር ነበሩ፤ ከእነርሱም ጋር አብረን ቆርኔሌዎስ ወደ ተባለው ሰው ቤት ገባን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 መንፈስ ቅዱስም ምንም ሳላወላውል ከእነርሱ ጋራ እንድሄድ ነገረኝ። እነዚህም ስድስት ወንድሞች ከእኔ ጋራ ሄዱ፤ ወደ ሰውየውም ቤት ገባን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 መንፈስም ሳልጠራጠር ከእነርሱ ጋር እሄድ ዘንድ ነገረኝ። እነዚህም ስድስቱ ወንድሞች ደግሞ ከእኔ ጋር መጡ፤ ወደዚያ ሰውም ቤት ገባን። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 መንፈስ ቅዱስም፦ ‘ሳትጠራጠር አብረሃቸው ሂድ’ አለኝ፤ እነዚህ ስድስቱ ወንድሞቻችንም ተከትለውኝ መጡና ወደዚያ ሰው ቤት ገባን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 መንፈስም ሳልጠራጠር ከእነርሱ ጋር እሄድ ዘንድ ነገረኝ። እነዚህም ስድስቱ ወንድሞች ደግሞ ከእኔ ጋር መጡ ወደዚያ ሰውም ቤት ገባን። 参见章节 |