Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 23:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዳዊትም አገሩን በመናፈቅ “በቤተልሔም ቅጽር በር አጠገብ ካለው የውሃ ጒድጓድ የምጠጣው ውሃ የሚያመጣልኝ ሰው ምነው ባገኘሁ!” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዳዊትም በናፍቆት፣ “በቤተ ልሔም በር አጠገብ ካለችው ጕድጓድ ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዳዊትም በናፍቆት፥ “በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ጉድጓድ ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳዊ​ትም፥ “በበሩ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠ​ጣኝ?” ብሎ ተመኘ። ያን​ጊ​ዜም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ኀይል በቤተ ልሔም ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዳዊትም፦ በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠጣኝ? ብሎ ተመኘ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 23:15
12 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ወዲያውኑ ራሔል ሞተች፤ አሁን ቤተ ልሔም ተብሎ በሚጠራው ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ ዳር ተቀበረች።


ስለዚህ ዝነኞች የሆኑት ሦስቱ ኀያላን ወታደሮች የፍልስጥኤማውያንን ሰፈር በድፍረት ጥሰው በማለፍ ከጒድጓዱ ውሃ ቀድተው ለዳዊት ይዘውለት መጡ፤ ዳዊት ግን ሊጠጣ አልወደደም፤ ይህንንም በማድረግ ፈንታ ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ካፈሰሰው በኋላ፥


ዳዊትም “በቤተልሔም ቅጽር በር አጠገብ ካለው የውሃ ጒድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን በሰጠኝ!” ብሎ ተመኘ።


የአንተን አዳኝነት በሙሉ ልቤ እመኛለሁ። እምነቴን በቃልህ ላይ አድርጌአለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች።


“ድኾችና ችግረኞች ውሃ ይፈልጋሉ፤ አያገኙም፤ ጒሮሮአቸው ከጥማት የተነሣ ሲደርቅ፥ እኔ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን እሰማለሁ፤ እኔም የእስራኤል አምላክ ከቶ አልተዋቸውም።


“ለተጠማው ምድር ውሃን እሰጣለሁ፤ በደረቀውም ምድር ጅረቶች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤ መንፈሴን በልጆችህ ላይ አፈሳለሁ፤ በረከትንም ለልጅ ልጆችህ እሰጣለሁ።


ኢየሱስም “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ውሃ አጠጪኝ!’ የሚልሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂው ኖሮ፥ እርሱን መለመን የሚገባሽ አንቺ ነበርሽ፤ እርሱም የሕይወትን ውሃ ይሰጥሽ ነበር” አላት።


እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘለዓለም ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ፥ ለሚጠጣው ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል።”


የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “ውሃ የጠማው ቢኖር ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፤


跟着我们:

广告


广告