Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 20:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ኢዮአብ የእስራኤል ሠራዊት አዛዥ ሲሆን፥ የዮዳሄ ልጅ በናያ የዳዊት ክብር ዘብ ኀላፊ ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ኢዮአብ በእስራኤል ሰራዊት ሁሉ ላይ የበላይ ሆነ፤ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ኢዮአብ በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አዛዥ ሆነ፤ የዮዳሄ ልጅ በናያ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊያታውያን ላይ አዛዥ ሆነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ኢዮ​አ​ብም በእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በና​ያስ በከ​ሊ​ታ​ው​ያ​ንና በፈ​ሊ​ታ​ው​ያን ላይ አለቃ ነበረ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበር፥ የዩዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፥

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 20:23
10 交叉引用  

ስለዚህ የኢዮአብ ወታደሮች፥ የንጉሡ የክብር ዘበኞችና ሌሎች ወታደሮችም ከአቢሳ ጋር ከኢየሩሳሌም ወጥተው የቢክሪን ልጅ ሼባዕን በመከታተል አሳደዱት።


ሌላው ዝነኛ ወታደር የቃብጽኤል ተወላጅ የነበረው የዮዳሄ ልጅ በናያ ነበር፤ እርሱም ሁለት የታወቁ ሞአባውያን ወታደሮችን ከመግደሉም ሌላ ብዙ የጀግንነት ሥራ ፈጽሞአል፤ አንድ ጊዜ በምድር ላይ ዐመዳይ በወረደበት ቀን ወደ አንድ ዋሻ ወርዶ አንበሳ ገደለ፤


በዚህ ዐይነት ዳዊት የመላው እስራኤል ንጉሥ ሆኖ ሕዝቡ ዘወትር ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት እንዲችል ጥረት ያደርግ ነበር፤


ስለዚህም ጉዳይ ከጸሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ተመካከረ፤ እነርሱም ዓላማውን ደገፉ፤


ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፥ የዮዳሄ ልጅ በናያ፥ ነቢዩ ናታን፥ ሺምዒ፥ ሬዒና የዳዊት የክብር ዘበኞች አዶንያስን አልደገፉም።


ንጉሡ ሰሎሞን በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤


ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኀላፊዎች ወደሆኑት የጦር መኰንኖች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸውና፥


跟着我们:

广告


广告