Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 20:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በከተማይቱ ውስጥ የምትኖር አንዲት ብልኅ ሴት በቅጽሩ ላይ ሆና ድምፅዋን ከፍ በማድረግ “ስሙ! ስሙ! ኢዮአብ ወደዚህ ይመጣ ዘንድ ንገሩት፤ እኔ ላነጋግረው እፈልጋለሁ!” አለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አንዲት ብልኅ ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ከከተማ ትጣራለች፤ “ስሙ! ስሙ! ለኢዮአብ የምነግረው ነገር ስላለ ወደዚህ እንዲመጣ ንገሩት” አለቻቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚያ አንዲት ብልኅ ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፥ “ስሙ! ስሙ! ኢዮአብን ላነጋግርህ እንድችል ወደዚህ ና በሉት” አለቻቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከቅ​ጥ​ሩም አን​ዲት ብል​ሃ​ተኛ ሴት፥ “ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮ​አ​ብ​ንም፦ እነ​ግ​ርህ ዘንድ ወደ​ዚህ ቅረብ በሉት” ስትል ጮኸች። ወደ እር​ስ​ዋም ቀረበ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከከተማይቱም አንዲት ብልሃተኛ ሴት፦ ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮአብንም፦ እነግርህ ዘንድ ወደዚህ ቅረብ በሉት ስትል ጮኸች።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 20:16
7 交叉引用  

ስለዚህም በተቆዓ የምትኖረውን አንዲት ብልኅ ሴት አስጠራ፤ እርስዋም በደረሰች ጊዜ “ሐዘንተኛ ለመምሰል ሞክሪ፤ የሐዘን ልብስሽን ልበሺ፤ ቅቤም አትቀቢ፤ ለብዙ ጊዜ በሐዘን ላይ የቈየሽ ሴት ለመምሰል ተዘጋጂ፤


ኢዮአብ ወደዚያ በሄደ ጊዜም ሴትዮዋ “ኢዮአብ የምትባለው አንተ ነህን?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” አላት። እርስዋም “ጌታዬ፥ እስቲ አድምጠኝ” አለችው፤ እርሱም “እነሆ፥ አዳምጥሻለሁ” አላት።


ይህንንም ዕቅድ በተግባር ለመግለጥ ወደ ከተማይቱ ሕዝብ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሺባዕን ራስ ቈርጠው በግንቡ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ እርሱም ወታደሮቹ ከተማይቱን ለቀው ይወጡ ዘንድ ምልክት እንዲሆን እምቢልታ ነፋ፤ እነርሱም ወደየቤታቸው ተመለሱ፤ ኢዮዓብም ንጉሡን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ።


ውሳኔውን በሥራ ላይ እንዲያውል የተመደበው አርዮክ የተባለው የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ነበር፤ ስለዚህ ዳንኤል ወደ እርሱ ሄደና በዘዴ አነጋገር፦


跟着我们:

广告


广告