Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 20:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከኢዮአብ ወታደሮች አንዱ በዐማሳ ሬሳ አጠገብ ቆሞ “ኢዮአብንና ዳዊትን የምትከተሉ ሁሉ ኢዮአብን ተከተሉ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በአሜሳይ ሬሳ አጠገብ ከቆሙት ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ፤ “ኢዮአብን የሚወድድ፣ የዳዊትም የሆነ ሁሉ ኢዮአብን ይከተል!” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በአማሳይ ሬሳ አጠገብ ከቆሙት ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ፤ “ኢዮአብን የሚወድ፥ የዳዊትም የሆነ ሁሉ ኢዮአብን ይከተል!” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከኢ​ዮ​አ​ብም ብላ​ቴ​ኖች አንዱ በአ​ሜ​ሳይ ሬሳ አጠ​ገብ ቆሞ፥ “ኢዮ​አብ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? የዳ​ዊ​ትም የሆኑ ኢዮ​አ​ብን የሚ​ከ​ተሉ እነ​ማን ናቸው?” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን አሳደዱ። ከኢዮአብም ብላቴኖች አንዱ በአሜሳይ ሬሳ አጠገብ ቆሞ፦ ለኢዮአብ ወዳጅ የሚሆን ለዳዊትም የሆነ ሁሉ ኢዮአብን ይከተል ይል ነበር።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 20:11
6 交叉引用  

የዐማሳ ሬሳ በደም እንደ ተበከለ በመንገዱ መካከል ተዘርሮ ነበር፤ ያም ሰው የኢዮአብ ወታደር ሁሉ ቆሞ ሲመለከት አይቶ ሬሳውን በመጐተት ወደ እርሻ ወሰደውና በልብስ ሸፈነው።


ሬሳው ከመንገዱ መካከል ከተነሣ በኋላ ሰዎች ሁሉ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ለማሳደድ ኢዮአብን ተከትለው ሄዱ።


የእኛ ዕቅድ ይህ አይደለም፤ የተራራማው የኤፍሬም አገር ተወላጅ የሆነ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ የቢክሪ ልጅ በንጉሥ ዳዊት ላይ ዐመፅ አስነሥቶአል፤ ብቻ ይህ ሰው ይሰጠኝ እንጂ እኔ ከተማይቱን ለቅቄ እሄዳለሁ።” እርስዋም “ራሱን ቈርጠን በግንብ ላይ እንወረውርልሃለን” አለችው።


ንጉሡም ዐማሣን “የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠርተህ በአንድነት ሰብስብና ከነገ ወዲያ ይዘሃቸው ወደዚህ ተመለስ” አለው።


ኢዩ ቀና ብሎ ወደ ላይ በመመልከት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከእኔ ጋር የሚተባበር ማን ነው?” ሲል ጮኸ፤ ቊጥራቸው ከሁለት እስከ ሦስት የሆነ የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በመስኮት ብቅ ብለው ወደ እርሱ ተመለከቱ፤


跟着我们:

广告


广告