Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 19:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ደግሞም ንጉሡ ይህን ያኽል ታላቅ ወሮታ የሚከፍለኝ ለምንድን ነው? ነገር ግን የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሬ ከአንተ ጋር ጥቂት መንገድ ብቻ እሄዳለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 አገልጋይህ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ከንጉሡ ጋራ ጥቂት መንገድ ይሄዳል፤ ነገር ግን ንጉሡ በዚህ ሁኔታ ወሮታ የሚመልስልኝ ለምንድን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፤ ታዲያ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? ከእንግዲህ አገልጋይህ የሚበላውንና የሚጠጣውን ጣዕሙን መለየት ይችላል? የሚዘፍኑትን የወንዶችና የሴቶችን ድምፅ አሁንስ መስማት እችላለሁ? ታዲያ አገልጋይህ ለንጉሥ ጌታዬ ለምን ተጨማሪ ሸክም ይሆናል?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እኔ ባሪ​ያህ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግሬ ከን​ጉሡ ጋር ጥቂት ልሄድ ነበር፤ ንጉሡ እን​ዲህ ያለ ወረታ ለምን ይመ​ል​ስ​ል​ኛል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እኔ ባሪያህ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ከንጉሡ ጋር ጥቂት ልሄድ ነበር፥ ንጉሡ እንዲህ ያለ ወረታ ለምን ይመልስልኛል?

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 19:36
5 交叉引用  

እነሆ፥ እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሰው ነኝ፤ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? የምበላውንም ሆነ የምጠጣውን ጣዕም መለየት እችላለሁን? ጆሮዬም የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት ይችላልን? ንጉሥ ሆይ! በጌታዬ ላይ ለምን ተጨማሪ ሸክም እሆንብሃለሁ?


ከዚያም በኋላ እኔ አገልጋይህ ወደ ቤቴ ተመልሼ እንድሄድና በወላጆቼ መቃብር አጠገብ እንዳርፍ ፍቀድልኝ፤ እነሆ፥ ይህ ልጄ ኪምሀም ያገለግልሃል፤ ንጉሥ ሆይ! እርሱን ይዘኸው ሂድ፤ የወደድከውንም ለእርሱ አድርግለት።”


ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን።


በወጣትነትህ ዘመን ፈጣሪህን አስብ፤ ይህን ባታደርግ ግን ክፉ ቀን ይመጣብሃል፤ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመቶች ይደርሳሉ።


ስጡ፤ ለእናንተም ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ እንዲሁ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም በጥሩ መስፈሪያ ታምቆና ተጠቅጥቆ እስኪትረፈረፍ ድረስ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል።”


跟着我们:

广告


广告