Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 19:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 መፊቦሼት ከኢየሩሳሌም ተነሥቶ ንጉሡን በሚቀበልበት ስፍራ በደረሰ ጊዜ ንጉሡ “መፊቦሼት ሆይ፥ ስለምን ከእኔ ጋር ሳትሄድ ቀረህ?” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እርሱም ንጉሡን ለመቀበል ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፣ “ሜምፊቦስቴ፣ ዐብረኸኝ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የሳኦል ልጅ መፊቦሼትም ንጉሡን ለመቀበል ወረደ። ንጉሡ ከተሰደደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተመለሰበት ዕለት ድረስ ለእግሩ መጫሚያ አላደረገም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከዚ​ህም በኋላ ንጉ​ሡን ሊቀ​በ​ለው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ፥ ከእኔ ጋር ስለ​ምን አል​ወ​ጣ​ህም?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ንጉሡም ሊቀበለው ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ ከእኔ ጋር ስለ ምን አልወጣህም? አለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 19:25
3 交叉引用  

አቤሴሎምም “ለወዳጅህ ለዳዊት የነበረህ ታማኝነት እንደዚህ ነበርን? እርሱንስ ተከትለህ ለምን አልሄድክም?” ሲል ጠየቀው።


ሌላው የሳኦል ዘር የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ሲሆን፥ እርሱ ሳኦልና ዮናታን በተገደሉ ጊዜ ገና የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ የእነርሱን ሞት የሚገልጠው ወሬ ከኢይዝራኤል ከተማ በተነገረ ጊዜ ሞግዚቱ እርሱን ይዛ ሸሸች፤ ነገር ግን በጥድፍያ በምትሸሽበት ጊዜ ከእጅዋ ወደቀ፤ ከዚህም የተነሣ ሽባ ሆነ።


የሳኦል የልጅ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት በመጣ ጊዜ በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት አክብሮቱን ገለጠ። ዳዊትም “መፊቦሼት!” ሲል ጠራው። መፊቦሼትም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።


跟着我们:

广告


广告