Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ንጉሡም “እናንተ መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አደርጋለሁ” ሲል መለሰላቸው። ከዚህ በኋላም በቅጽር በሩ አጠገብ ቆሞ በሺህና በመቶ የተመደቡት ሠራዊት ተሰልፈው ሲወጡ ተመለከተ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ንጉሡም፣ “መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አደርጋለሁ” አላቸው። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ በመቶና በሺሕ እየሆነ ተሰልፎ ሲወጣ፣ ንጉሡ በቅጥሩ በር ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ንጉሡም፥ “መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አደርጋለሁ” አላቸው። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ በመቶና በሺህ እየሆነ ተሰልፎ ሲወጣ፥ ንጉሡ በቅጥሩ በር ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ንጉ​ሡም፥ “በፊ​ታ​ችሁ መል​ካም የሚ​መ​ስ​ላ​ች​ሁን አደ​ር​ጋ​ለሁ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም በበሩ አጠ​ገብ ቆመ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መቶ በመቶ፥ ሺህ በሺህ እየ​ሆኑ ወጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ንጉሡም፦ መልካም የሚመስላችሁን አደርጋለሁ አላቸው። ንጉሡም በበሩ አጠገብ ቆመ፥ ሕዝቡም ሁሉ መቶ በመቶ ሺህ በሺህ እየሆኑ ወጡ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:4
5 交叉引用  

ንጉሥ ዳዊት ተከታዮቹን ሁሉ በአንድነት ከሰበሰበ በኋላ በሺህና በመቶ መድቦ ለእያንዳንዱ ቡድን የጦር መኰንን ሾመ፤


ዳዊት በከተማይቱ ውስጣዊና ውጫዊ በሮች መካከል ባለው ግልጥ ቦታ ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂው በቅጥሩ በኩል ወደ ማማው ወጥቶ ስለ ነበር ቀና ብሎ ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤


ለኢዮአብ፥ ለአቢሳና ለኢታይም “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ በአቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት” የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፤ ዳዊት ይህን ትእዛዝ ለጦር አዛዦቹ በሰጠ ጊዜም ወታደሮቹ ሁሉ ይሰሙ ነበር።


በዳኝነት ለሚያገለግሉት የፍትሕ ጥበብ ይሰጣቸዋል፤ የከተማይቱን የቅጽር በሮች ከጠላት ለሚከላከሉትም ኀይልን ይሰጣቸዋል።


አምስቱም የፍልስጥኤም ነገሥታት በመቶና በሺህ ከተመደቡ ሰልፈኞቻቸው ጋር ዘመቱ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም የአኪሽ ደጀን ጦር ሆነው ዘመቱ፤


跟着我们:

广告


广告