Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አሒማዓጽም “ጌታዬ ሆይ፥ የጦር አዛዥህ ኢዮአብ ወደ አንተ በላከኝ ጊዜ ታላቅ ሁካታ ሆኖ አየሁ፤ ነገር ግን ምን እንደ ሆነ መናገር አልችልም” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ንጉሡም፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አኪማአስም፣ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም ባሪያህን ሊልክ ሲል፣ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ንጉሡም፥ “ወጣቱ አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አሒማዓጽም፥ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም አገልጋይህን ሊልክ ሲል፥ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ንጉ​ሡም፥ “ብላ​ቴ​ናው አቤ​ሴ​ሎም ደኅና ነውን?” አለ። አኪ​ማ​ሖ​ስም፥ “ኢዮ​አብ እኔን ባሪ​ያ​ህ​ንና የን​ጉ​ሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ብዙ ሰዎ​ችን አይ​ቻ​ለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ንጉሡም፦ ብላቴናው አቤሴሎም ደህና ነውን? አለ። አኪማአስም፦ ኢዮአብ እኔን ባሪያህንና የንጉሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ትልቅ ሽብር አይቻለሁ፥ ምን እንደሆነ ግን አላወቅሁም ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:29
6 交叉引用  

አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው።


ንጉሡም “እልፍ ብለህ ቁም” አለው። እርሱም እልፍ ብሎ ቆመ።


ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አገልጋዩም “ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ላይ የደረሰ ነገር በጠላቶችህና በአንተ ላይ በዐመፁት ሁሉ ላይ ይድረስ!” ሲል መለሰ።


ኢዮአብም ዐማሣን “ወዳጄ ሆይ! እንደምንድን ነህ?” አለውና የሚስመው በማስመሰል ሪዙን በቀኝ እጁ ያዘ፤


ፈጠን ብለህ ሂድና የእርስዋን፥ የባልዋንና የልጅዋን ደኅንነት ጠይቃት” አለው። እርስዋም ግያዝን “ሁላችንም ደኅና ነን” ስትል ነገረችው።


跟着我们:

广告


广告