2 ሳሙኤል 17:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ሰው የጦር አዛዥ አድርጎ ሾመ፤ ዐማሣ የእስራኤላዊው የዬቴር ልጅ ነበር፤ እናቱም አቢጌል ተብላ የምትጠራ የናሐሽ ልጅ ስትሆን ለኢዮአብ እናት ለጸሩያ እኅት ነበረች። ዜና መ. 2፥17 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፣ የጽሩያን እኅት፣ የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አማሳይን በሠራዊቱ ላይ ሾመ፤ አማሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፥ የጽሩያን እኅት፥ የናዖስን ልጅ አቢግያንሰ አግብቶ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 አቤሴሎምም በሠራዊቱ ላይ በኢዮአብ ስፍራ አሜሳይን ሾመ፤ አሜሳይም የኢዮአብን እናት የሶርህያን እኅት የነዓሶንን ልጅ አቢግያን የአገባው የኢይዝራኤላዊው የዮቶር ልጅ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 አቤሴሎምም በጭፍራው ላይ በኢዮአብ ስፍራ አሜሳይን ሾመ፥ አሜሳይም የይስማኤላዊ ሰው የዬቴር ልጅ ነበረ፥ እርሱም የኢዮአብን እናት የጽሩያን እኅት የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር። 参见章节 |