Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 17:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜም አደጋ እጥልበታለሁ፤ ሽብር እለቅበታለሁ፤ ከዚያም ዐብሮት ያለው ሕዝብ ሁሉ ትቶት ይሸሻል፤ ንጉሡን ብቻ እመታዋለሁ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በደከመውና በዛለ ጊዜም ሽብር እለቅበታለሁ፤ አብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ ትቶት ይሸሻል፤ ንጉሡን ብቻውን እመታዋለሁ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ደክ​ሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወ​ድ​ቅ​በ​ታ​ለሁ፤ አስ​ፈ​ራ​ው​ማ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸ​ሻል፤ ንጉ​ሡ​ንም ብቻ​ውን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ደክሞና እጅ ዝሎ ሳለ እወድቅበታለህ፥ አስፈራውማለሁ፥ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸሻል፥ ንጉሡንም ብቻውን እመታዋለሁ፥

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 17:2
10 交叉引用  

ንጉሡና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዕረፍት አደረጉ።


ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቈይ አኪጦፌል አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዛሬ ማታ ዳዊትን አሳድጄ ለመያዝ እችል ዘንድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች እንድመርጥ ፍቀድልኝ፤


የሶርያ ንጉሥ “በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ” ሲል ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትእዛዝ አስተላለፈ፤


ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ምሕረት አታድርግላቸው፤ የፈረሰውን በመሥራታችን በስድብ አዋርደውናልና በደላቸውን አትርሳ።”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ እንግደለውና ርስቱን እኛ እንውረስ!’ ተባባሉ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ፥ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ ‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ ተብሎ ተጽፎአልና በዚህች ሌሊት፥ ሁላችሁም ትክዱኛላችሁ።


ሕዝብ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝብ ቢሞት ለእናንተ የሚሻል መሆኑን ከቶ አልተገነዘባችሁምን?”


እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ አይደሉም፤ አንተ በጒዞ ላይ ደክሞህ በነበረ ጊዜ በኋላ በኩል አደጋ ጣሉብህ፤ ደክመው ወደ ኋላ ያዘግሙ የነበሩትንም ሁሉ ገደሉ።


跟着我们:

广告


广告