Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 15:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በአቤሴሎም ጋባዥነት ከእርሱ ጋር ከኢየሩሳሌም የሄዱ ሁለት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ተከትለውት የሄዱት ስለ ሤራው ምንም ነገር ሳያውቁ በቅንነት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከኢየሩሳሌምም ሁለት መቶ ሰዎች አቤሴሎም ሄዱ፤ በእንግድነት ተጋብዘው በየዋህነት ከመሄዳቸው በቀር፣ ስለ ጕዳዩ የሚያውቁት አንዳችም ነገር አልነበረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከአቤሴሎም ጋር ከኢየሩሳሌምም ሁለት መቶ ሰዎች አብረውት ሄደው ነበር፤ በእንግድነት ተጋብዘው በቅንነት ከመሄዳቸው በስተቀር፥ ስለጉዳዩ ምንም ነገር አያውቁም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የተ​ጠ​ሩ​ትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም በየ​ዋ​ህ​ነት ሄዱ፤ ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ከቶ አያ​ው​ቁም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሴሎም ጋር በየዋህነት ከኢየሩሳሌም ሄዱ፥ የሚሆነውንም ነገር ከቶ አያውቁም ነበር።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 15:11
8 交叉引用  

እኅቴ ነች ያለኝ ራሱ አብርሃም ነው፤ እርስዋም ወንድሜ ነው ብላኛለች፤ እኔ ይህን ያደረግኹት በቅንነትና በንጹሕ ኅሊና ስለ ሆነ ምንም በደል አልፈጸምኩም” አለ።


ሞኝ ሰው የሚነግሩትን ሁሉ አምኖ ይቀበላል፤ ብልኆች ግን እርምጃቸውን በጥንቃቄ ይመረምራሉ።


ብልኅ ሰው አደጋ ሲመጣ አይቶ ይሸሸጋል። ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ሰተት ብሎ ወደ መከራ በመግባት ይጐዳል።


“እነሆ! እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች፥ እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ።


በውኑ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ መጠየቅ ይህ ዛሬ የመጀመሪያ ጊዜዬ ነውን? አይደለም! ንጉሥ ሆይ! እኔን አገልጋይህንም ሆነ ቤተሰቤን በዚህ ጉዳይ ላይ አትውቀስ፤ ስለዚህ ጉዳይ ይብዛም ይነስም እኔ የማውቀው ነገር የለም።”


ወደ ከተማው እንደ ገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ፤ መሥዋዕቱን መባረክ ስላለበት ሕዝቡ እርሱ ከመምጣቱ በፊት አይበሉም፤ ከዚያም በኋላ ተጋባዦቹ ይበላሉ፤ ፈጥናችሁ ውጡ፤ አሁን ታገኙታላችሁ” አሉአቸው።


跟着我们:

广告


广告