Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 10:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ዐሞናውያንም የሶርያውያንን መሸሽ ባዩ ጊዜ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ አፈገፈጉ። ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ዐሞናውያንን መውጋት አቁሞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሶርያውያን መሸሻቸውን አሞናውያን ባዩ ጊዜ፣ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማዪቱ ውስጥ ገቡ። ስለዚህም ኢዮአብ አሞናውያንን መውጋቱን አቁሞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሶርያውያን መሸሻቸውን አሞናውያን ባዩ ጊዜ፥ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማዪቱ ውስጥ ገቡ። ስለዚህም ኢዮአብ አሞናውያንን መውጋቱን አቁሞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የአ​ሞን ልጆ​ችም ሶር​ያ​ው​ያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነ​ርሱ ደግሞ ከአ​ቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ገቡ፤ ኢዮ​አ​ብም ከአ​ሞን ልጆች ዘንድ ተመ​ልሶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የአሞንም ልጆች ሶርያውያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፥ ወደ ከተማይቱም ገቡ፥ ኢዮአብም ከአሞን ልጆች ዘንድ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 10:14
7 交叉引用  

ሶርያውያን በእስራኤላውያን ድል እንደ ተመቱ በተገነዘቡ ጊዜ ሠራዊታቸውን ሁሉ በአንድነት አሰባሰቡ፤


የዓመት መጀመሪያ በሆነው በጸደይ ወራት፥ በተለምዶ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚዘምቱበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከጦር መኰንኖቹና ከመላው የእስራኤል ሠራዊት ጋር አዘመተው፤ እነርሱም ዐሞናውያንን ድል ነሥተው ራባ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቈየ።


ስለዚህ ንጉሡ አቢሳን “ሼባዕ ከአቤሴሎም ይበልጥ የከፋ ችግር ይፈጥርብናል፤ ወታደሮቼን ይዘህ ተከታተለው፤ አለበለዚያ የተመሸጉ ከተሞቼን ይዞ ከእኛ እጅ ሊያመልጥ ይችላል” አለው።


ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ ሳላጠፋቸውም ወደ ኋላ አልመለስም፤


የጽሩያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ ዝነኞች የሆኑት የሠላሳዎቹ ወታደሮች አለቃ ነበር፤ እርሱም ጦሩን አንሥቶ ከሦስት መቶ ሰዎች ጋር በመዋጋት ሁሉንም ገደለ፤ ስለዚህም እንደ ሦስቱ ዝነኛ ሆነ።


የጸሩያ ልጅ አቢሳ ኤዶማውያንን በጨው ሸለቆ ውስጥ ድል አድርጎ ከእነርሱ መካከል ዐሥራ ስምንት ሺህ የሚሆኑትን ገደለ፤


跟着我们:

广告


广告