Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ኤልሳዕም ግያዝን “ሱነማይቱን ጥራ” አለው፤ እርስዋም በመጣች ጊዜ ኤልሳዕ “ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ኤልሳዕም ግያዝን ጠርቶ፣ “ሱነማዪቱን ጥራት፤” አለው፤ እርሱም ጠራት። እንደ መጣችም፣ “በይ ልጅሽን ውሰጂ” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ኤልሳዕም ግያዝን “ሱነማይቱን ጥራ” አለው፤ እርሷም በመጣች ጊዜ ኤልሳዕ “ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ግያ​ዝ​ንም ጠርቶ፥ “ይህ​ችን ሱማ​ና​ዊት ጥራ” አለው። ጠራ​ትም፤ ወደ እር​ሱም በገ​ባች ጊዜ፥ “ልጅ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ውሰጂ” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ግያዝንም ጠርቶ “ይህችን ሱነማዊት ጥራ፤” አለው። ጠራትም፤ ወደ እርሱም በገባች ጊዜ “ልጅሽን አንሥተሽ ውሰጂ፤” አላት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:36
8 交叉引用  

አንዲት ቈንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፍለጋ ተደረገ፤ ሹኔም ተብላ ከምትጠራው ስፍራ አቢሻግ የምትባል አንዲት ልጃገረድ አግኝተው ለንጉሡ አመጡለት፤


ኤልያስ ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ በመስጠት “ተመልከቺ፤ እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል!” አላት።


ኤልሳዕም ተነሥቶ በክፍሉ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ጀመር፤ እንደገናም ተመለሰና በመዘርጋት በልጁ ላይ ተጋደመ፤ ልጁም ሰባት ጊዜ ካስነጠሰው በኋላ ዐይኖቹን ከፈተ።


እርስዋም ወደ መሬት ለጥ ብላ በኤልሳዕ ጫማ ላይ በመውደቅ እጅ ነሣች፤ ከዚያም በኋላ ልጅዋን ይዛ ሄደች።


ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “አውጥተህ ውሰድ” አለው፤ ሰውየውም ጐንበስ ብሎ አነሣው።


ልጅዋን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቈይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።”


የሞተው ቀና ብሎ ተቀመጠና መነጋገር ጀመረ፤ ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለእናትዮዋ፥ “እነሆ፥ ልጅሽ፤” ብሎ ሰጣት፤


ሴቶች የሞቱባቸውን ዘመዶቻቸውን ከሞት ተነሥተው አገኘአቸው። ሌሎችም የበለጠ ትንሣኤ ለማግኘት አስበው ልዩ ልዩ ሥቃይ ተቀበሉ፤ ከእስራት ነጻ መሆንንም አልፈቀዱም።


跟着我们:

广告


广告