Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እርስዋም አህያው እንዲጫንላት ካደረገች በኋላ አገልጋዩን “በሚቻል መጠን አህያው እንዲፈጥን አድርግ፤ እኔም ካልነገርኩህ በቀር ቀስ ብሎ እንዲሄድ ፋታ አትስጠው” ስትል አዘዘችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚያም አህያውን ጭና አገልጋይዋን፣ “ቶሎ ቶሎ ንዳ፤ እኔ ካልነገርኩህ በቀር ለእኔ ብለህ አታዝግም” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሷም አህያው እንዲጫንላት ካደረገች በኋላ አገልጋዩን “በሚቻል መጠን አህያው እንዲፈጥን አድርግ፤ እኔም ካልነገርኩህ በቀር ቀስ ብሎ እንዲሄድ ፋታ አትስጠው” ስትል አዘዘችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አህ​ያ​ው​ንም አስ​ጭና ሎሌ​ዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላ​ዝ​ዝህ አታ​ዘ​ግ​የኝ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ቄር​ሜ​ሎስ ተራራ እን​ሂድ” አለ​ችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አህያውንም አስጭና ሎሌዋን “ንዳ፤ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤” አለችው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:24
7 交叉引用  

አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ።


ከዚህም በኋላ እርሱ “አህያዬን ጫኑልኝ!” አላቸው፤ ልጆቹም አህያውን ጭነውለት ሽማግሌው ነቢይ በአህያው ላይ ተቀምጦ፥


ከተመገቡም በኋላ ሽማግሌው ነቢይ ከይሁዳ መልሶ ላመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ አህያውን ጫነለት፤


ባልዋ ግን “ዛሬ ስለምን ትሄጂአለሽ? ሰንበት ወይም የጨረቃ በዓል የሚከበርበት ጊዜ አይደለም” አላት። እርስዋም “ግድ የለም፤ እንዳልኩህ አድርግ” አለችው፤


እርስዋም ከዚያ ተነሥታ ኤልሳዕ ወደነበረበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣች። ኤልሳዕም ገና በሩቅ ሳለች ወደ እርሱ ስትመጣ አይቶ አገልጋዩን ግያዝን “ተመልከት! ያቺ ሴት ከሱነም ወደዚህ በመምጣት ላይ ናት!


ስለዚህም ሙሴ ሚስቱንና ወንዶች ልጆቹን በአህያ ላይ አስቀምጦ ወደ ግብጽ መጓዝ ጀመረ፤ ተአምራት የሚገለጥበት የእግዚአብሔርንም በትር በእጁ ይዞ ነበር።


跟着我们:

广告


广告