Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ባልዋንም ጠርታ “አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ዘንድ መሄድ ይገባኛል፤ በተቻለም መጠን ፈጥኜ እመለሳለሁ” አለችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም ባሏን ጠርታ፣ “ወደ እግዚአብሔር ሰው በፍጥነት ደርሼ እንድመለስ አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝ” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ባሏንም ጠርታ “አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ዘንድ መሄድ ይገባኛል፤ በተቻለም መጠን ፈጥኜ እመለሳለሁ” አለችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ባል​ዋ​ንም ጠርታ፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ዘንድ በፍ​ጥ​ነት እሄ​ዳ​ለ​ሁና አንድ ሎሌና አንድ አህያ ላክ​ልኝ” አለ​ችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ባልዋንም ጠርታ “ወደ እግዚአብሔር ሰው በፍጥነት ደርሼ እመለስ ዘንድ አንድ ሎሌና አንድ አህያ ላክልኝ፤” አለችው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:22
6 交叉引用  

እርሱንም አውጥታ ለኤልሳዕ በተሠራው ክፍል በማስገባት በአልጋው ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ተመልሳ ሄደች።


ባልዋ ግን “ዛሬ ስለምን ትሄጂአለሽ? ሰንበት ወይም የጨረቃ በዓል የሚከበርበት ጊዜ አይደለም” አላት። እርስዋም “ግድ የለም፤ እንዳልኩህ አድርግ” አለችው፤


እርስዋም አህያው እንዲጫንላት ካደረገች በኋላ አገልጋዩን “በሚቻል መጠን አህያው እንዲፈጥን አድርግ፤ እኔም ካልነገርኩህ በቀር ቀስ ብሎ እንዲሄድ ፋታ አትስጠው” ስትል አዘዘችው።


ፈጠን ብለህ ሂድና የእርስዋን፥ የባልዋንና የልጅዋን ደኅንነት ጠይቃት” አለው። እርስዋም ግያዝን “ሁላችንም ደኅና ነን” ስትል ነገረችው።


እኅትማማቾቹም “ጌታ ሆይ፥ ያ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ ኢየሱስ ላኩበት።


ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለ ነበረች በኢዮጴ ያሉት ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በልዳ መኖሩን ሰምተው “እባክህን ሳትዘገይ በቶሎ ድረስልን” ብለው ሁለት ሰዎች ላኩበት።


跟着我们:

广告


广告