Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 25:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ነገር ግን ምንም ሀብት የሌላቸውን የመጨረሻ ድኾች፥ አትክልት ኰትኳቾችና መሬት አራሾች ይሆኑ ዘንድ በይሁዳ ምድር ትቶአቸው ሄደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሆኖም የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ሌሎች የምድሪቱን ድኾች፣ ወይን ተካዮችና ዐራሾች እንዲሆኑ አስቀራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ነገር ግን ምንም ሀብት የሌላቸውን የመጨረሻ ድኾች፥ አትክልት ኰትኳቾችና መሬት አራሾች ይሆኑ ዘንድ በይሁዳ ምድር ትቶአቸው ሄደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የአ​በ​ዛ​ዎ​ችም አለቃ ከሀ​ገሩ ድሆች ወይን ተካ​ዮ​ችና አራ​ሾች እን​ዲ​ሆኑ አስ​ቀረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የዘበኞቹም አለቃ ከአገሩ ድሆች ወይን ተካዮችና አራሾች እንዲሆኑ አስቀረ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 25:12
10 交叉引用  

ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።


ናቡከደነፆር ኢኮንያንን አስሮ ከነእናቱ ከሚስቶቹ፥ ባለሟሎቹ ከሆኑ ባለሥልጣኖችና ከይሁዳ ታላላቅ ሰዎች ጋር በአንድነት ሰብስቦ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።


የባቢሎን ንጉሥ ሰባት ሺህ ለውጊያ ብቃት ያላቸው ወንዶችን፥ እንዲሁም አንድ ሺህ ብረት ቀጥቃጮችንና እደ ጥበበኞችን ወደ ባቢሎን ወሰደ።


የእድሳቱ ሥራ ባለቀ ጊዜም ቀሪው ገንዘብ ለንጉሥ ኢዮአስና ለካህኑ ዮዳሄ ተሰጠ፤ እነርሱም በዚህ ወርቅ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎትና ለመሥዋዕት የሚውሉ ሳሕኖችንና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ገዙ። ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ ዘወትር በቤተ መቅደስ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤


ከወንድሞቼ አንዱ ሐናኒ ተብሎ የሚጠራው ሌሎች ሰዎችን አስከትሎ ከይሁዳ ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ስለ ኢየሩሳሌምና ወደ ባቢሎን ተማርከው ከመወሰድ ስለ ተረፉትና በሕይወት ስላሉት አይሁድ ሁኔታ ጠየቅኋቸው።


ስለዚህም ርግማን ምድርን ያጠፋል፤ ሕዝቦችዋም በበደሉት በደል ተጠያቂዎች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይደመሰሳሉ፤ የሚተርፉትም ጥቂቶች ናቸው።


ምንም ሀብት ያልነበራቸውን ድኾች ብቻ በይሁዳ ምድር ተወ፤ ለእነርሱም የወይን ተክል ቦታዎችንና የሚያርሱት መሬት ሰጣቸው።


ከይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች ጥቂቶቹ ገና እጃቸውን አልሰጡም ነበር፤ እነርሱም የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን በሀገሪቱ ላይ ገዢ አድርጎ እንደ ሾመውና ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ በሀገሪቱ ለቀሩት ድኾች ኀላፊ ያደረገው መሆኑን ሰሙ፤


ነገር ግን በይሁዳ የመጨረሻ ድኾች የነበሩትን ሕዝብ ተወ፤ እነርሱም የወይን ተክል ኰትኳቾችና አራሾች እንዲሆኑ አደረገ።


“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ምድር በፈራረሱ ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ ‘አብርሃም ብቸኛ የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤ ምድሪቱ በሞላ ለእርሱ ተሰጠች፤ እኛ ግን እነሆ፥ ብዙዎች ነን፤ ምድሪቱም በእርግጥ በርስትነት ተሰጥታናለች።’


跟着我们:

广告


广告