Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 23:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ሊቀ ካህናቱ ሒልቂያ በቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው ሕግ ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው በማሰብ፥ ንጉሥ ኢዮስያስ ከኢየሩሳሌምና ከሌላውም የይሁዳ ከተማ ሁሉ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ሁሉ የቤተሰብ አማልክትን፥ ጣዖቶችንና ሌሎችንም አረማዊ የአምልኮ መፈጸሚያ ዕቃዎችን ሁሉ አስወገደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚህም በቀር ኢዮስያስ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን፣ የየቤተ ሰቡ ሰውን አማልክት፣ ጣዖታትን እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሊቀ ካህናቱ ሒልቂያ በቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው ሕግ ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው በማሰብ፥ ንጉሥ ኢዮስያስ ከኢየሩሳሌምና ከሌላውም የይሁዳ ከተማ ሁሉ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ሁሉ የቤተሰብ አማልክትን፥ ጣዖቶችንና ሌሎችንም አረማዊ የአምልኮ መፈጸሚያ ዕቃዎችን ሁሉ አስወገደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ደግ​ሞም ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባገ​ኘው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የሕ​ጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቹ​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ቹን ተራ​ፊ​ም​ንና ጣዖ​ታ​ት​ንም በይ​ሁዳ ሀገ​ርና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ገ​ኘ​ውን ርኵ​ሰት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያስ አስ​ወ​ገደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ደግሞም ካህኑ ኬልቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈውን የሕጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መናፍስት ጠሪዎቹንና ጠንቋዮቹን ተራፊምንና ጣዖታትንም በይሁዳ አገርና በኢየሩሳሌም የተገኘውን ርኵሰት ሁሉ ኢዮስያስ አስወገደ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 23:24
21 交叉引用  

ላባ በጎች ሊሸልት ሄዶ ስለ ነበር፥ እርሱ በሌለበት ራሔል በቤት የነበሩትን የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ ሄደች።


“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤


የአባቱንም መጥፎ አርአያነት ሁሉ ተከተለ፤ አባቱ ይሰግድላቸው የነበሩትንም ጣዖቶች አመለከ፤


ምናሴ አባቱ ሕዝቅያስ ደምስሶአቸው የነበሩትን የአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች እንደገና እንዲሠሩ አደረገ፤ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ባደረገውም ዐይነት ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሠዊያዎችን፥ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስልን ሠራ፤ የሰማይ ከዋክብትንም አመለከ።


የገዛ ልጁንም መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት በመሥራቱ የእግዚአብሔርን ቊጣ አነሣሣ።


ይሁን እንጂ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ተከበረ።


ግብጻውያን ተስፋ ይቈርጣሉ፤ ዕቅዳቸውም ተግባራዊ እንዳይሆን አደርጋለሁ፤ በዚህም ጊዜ እንዲረዱአቸው ጣዖቶቻቸውን ይጠይቃሉ፤ ሙታንን ወደሚጠሩ ጠንቋዮቻቸው ሄደው ይማከራሉ፤ ከሙታን መናፍስትም ምክር ይጠይቃሉ።


በዚሁ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ ወይም ያለ መሪ፥ ያለ መሥዋዕት ወይም ያለ ሐውልት፥ ያለ ልብሰ ተክህኖ ወይም የጣዖት ምስል ለብዙ ዘመን ይኖራሉ፤


“ከሙታን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ከጠንቋዮች ምክር አትጠይቁ፥ ይህን ብታደርጉ የረከሳችሁ ትሆናላችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


“ወንድ ወይም ሴት የሙታን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ይገደሉ፤ በድንጋይ ተወግረው ይገደሉ፤ በሞት የሚቀጡትም በራሳቸው በደል ነው።”


ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው።


ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ መርምሮ በእርሱ የሚጸና፥ እርሱንም ሰምቶ መርሳት ሳይሆን፥ በሥራ ላይ የሚያውለው ሰው በሥራው የተባረከ ይሆናል።


እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።


ይህ ሚካ የተባለ ሰው የራሱ የሆነ የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ በርከት ያሉ ጣዖቶች አንድ ኤፉድ ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው፤


跟着我们:

广告


广告