Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 23:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት፥ በኰረብቶች ላይ የተሠሩ መቃብሮችን አየ፤ በእነዚያም መቃብሮች ውስጥ የነበረውን ዐፅም ሁሉ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም ዐይነት መሠዊያው የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ኢዮስያስ ይህንን ሁሉ በማድረጉ ከብዙ ጊዜ በፊት በተደረገ የአምልኮ በዓል ላይ ንጉሥ ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ ነቢዩ የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ፤ ንጉሥ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት ይህን ትንቢት ተናግሮ የነበረው ነቢይ የተቀበረበትን መካነ መቃብር አይቶ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ኢዮስያስ ዘወር ሲል በኰረብታው ላይ የነበሩትን መቃብሮች አየ፤ ዐፅሞቹንም ከየመቃብሩ አስወጣ፤ ያ የእግዚአብሔር ሰው አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ መሠዊያውን ለማርከስ ሲል ዐፅሞቹን በላዩ ላይ አቃጠለበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት፥ በኰረብቶች ላይ የተሠሩ መቃብሮችን አየ፤ በእነዚያም መቃብሮች ውስጥ የነበረውን ዐፅም ሁሉ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም ዓይነት መሠዊያው የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ኢዮስያስ ይህንን ሁሉ በማድረጉ ከብዙ ጊዜ በፊት በተደረገ የአምልኮ በዓል ላይ ንጉሥ ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ ነቢዩ የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ፤ ንጉሥ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት ይህን ትንቢት ተናግሮ የነበረው ነቢይ የተቀበረበትን መካነ መቃብር አይቶ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ኢዮ​ስ​ያ​ስም ዘወር ብሎ በከ​ተ​ማው የነ​በ​ሩ​ትን መቃ​ብ​ሮች አየ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በበ​ዓል ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ ልኮ ከመ​ቃ​ብ​ሮቹ አጥ​ን​ቶ​ቹን አስ​ወጣ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይም አቃ​ጠ​ላ​ቸው፥ አረ​ከ​ሰ​ውም። ዘወ​ርም ብሎ ይህን ቃል ወደ ተና​ገ​ረው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መቃ​ብር ዐይ​ኖ​ቹን አቀና። እን​ዲ​ህም አለ፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ኢዮስያስም ዘወር ብሎ በተራራው የነበሩትን መቃብሮች አየ፤ ኢዮርብዓምም በበዓል ጊዜ በመሠዊያ አጠገብ ሲቆም እነዚህን ነገሮች የተነበየ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ልኮ፥ ከመቃብሮቹ አጥንቶቹን አስወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ አቃጠላቸው፤ አረከሰውም። ዘወርም ብሎ ወደ ተናገረው ወደ እግዚአብሔር ሰው መቃብር ዐይኖቹን አቅንቶ

参见章节 复制




2 ነገሥት 23:16
6 交叉引用  

በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይና በሰማርያ ታናናሽ ከተሞች በየኮረብታው ባሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይህ የእግዚአብሔር ነቢይ የተናገረው የትንቢት ቃል በእርግጥ ይፈጸማል።”


ንጉሥ ኢዮስያስ የድንጋይ ዐምዶችን ሁሉ ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስሎች አንከታክቶ ጣለ፤ እነርሱ ቆመውበት የነበረውንም ስፍራ የሙታን አጥንት ሞላበት።


የእስራኤል ሕዝብ ሬሳቸው በጣዖቶቻቸው ፊት እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ አጥንቶቻቸውንም በየመሠዊያቸው ዙሪያ እበትነዋለሁ።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።”


እንግዲህ ቅዱስ መጽሐፍን መሻር አይቻልም፤ የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን ቅዱስ መጽሐፍ አማልክት ብሎ ከጠራቸው


跟着我们:

广告


广告