Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፦

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ደግሞም ሰናክሬም፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋው መምጣቱን ሰማ፤ ይህንም እንደ ሰማ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞች ላከ፤ እንዲህም አለ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፦

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊወ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ተመ​ልሶ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እርሱም “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል፤” የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ደግሞ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን እንዲህ ሲል ላከ፤

参见章节 复制




2 ነገሥት 19:9
7 交叉引用  

ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቤንሀዳድ በከተማይቱ ወደሚገኘው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ፥ “ቤንሀዳድ እንዲህ ይላል ብሎ መልእክተኞችን ላከ፦


ይህ በዚህ እንዳለ የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከላኪሽ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ያም ሠራዊት ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፤


“የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሆይ፥ የምትታመንበት አምላክ ‘ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አትወድቅም’ ብሎ አያታልህ፤


የአሦር የጦር አዛዥ፥ የአሦር ንጉሥ ከሰፈሩ ከላኪሽ ተነሥቶ ሊብናን ሊያጠቃ እንደ ሄደ በመስማቱ እርሱም ወደዚያው ሄደ።


ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የክንፎች ድምፅ ለሚሰማባት አገር ወዮላት!


በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ የአሦር ንጉሥ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኛ እጅ ላከ፦


ይህ በዚህ እንዳለ ወዲያውኑ አንድ መልእክተኛ ደርሶ ሳኦልን “ፍልስጥኤማውያን አገሪቱን በመውረር ላይ ናቸውና አሁኑኑ ፈጥነህ ተመልሰህ ና!” አለው።


跟着我们:

广告


广告