Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 19:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እነሆ፤ የአሦር ነገሥታት በአገሮች ሁሉ ላይ ያደረጉትን፣ ፈጽሞም እንዳጠፏቸው ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነሆ፥ የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት በም​ድር ሁሉ ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን፥ እን​ዴ​ትስ እን​ዳ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ሰም​ተ​ሃል፤ አን​ተስ ትድ​ና​ለ​ህን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እነሆ፥ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን፥ እንዴትስ እንዳጠፋአቸው ሰምተሃል፤ አንተስ ትድናለህን?

参见章节 复制




2 ነገሥት 19:11
9 交叉引用  

የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።


የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ከንጉሠ ነገሥታቶቻችን እጅ አገሮቻቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እንግዲህ እናንተ ‘እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል’ ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?”


“የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሆይ፥ የምትታመንበት አምላክ ‘ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አትወድቅም’ ብሎ አያታልህ፤


የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዴንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?


የአሦር ንጉሠ ነገሥት የጻፈው ደብዳቤ “የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሕዝቦቻቸውን ከእኔ እጅ አላዳኑም፤ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድናቸው ከቶ አይችልም” በማለት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚዘልፍ ነበር፤


跟着我们:

广告


广告