Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 18:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ሕዝቅያስ ‘በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ ያድናችኋል፤ ከተማችንም በአሦርያውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል’ እያለ የሚሰብካችሁን አትስሙ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ደግሞም ሕዝቅያስ፣ ‘እግዚአብሔር በርግጥ ያድነናል፤ ይህች ከተማ ለአሦር ንጉሥ ዐልፋ አትሰጥም’ እያለ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ሕዝቅያስ ‘በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ ያድናችኋል፤ ከተማችንም በአሦርያውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል’ እያለ የሚሰብካችሁን አትስሙ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ር​ግጥ ያድ​ነ​ናል፤ ይህ​ች​ንም ከተማ የአ​ሦር ንጉሥ ሊይ​ዛት አይ​ች​ልም እያለ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ት​ታ​መኑ አያ​ድ​ር​ጋ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ሕዝቅያስም “እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል፤ ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም፤” ብሎ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 18:30
16 交叉引用  

በሕዝቅያስ አትታለሉ! እርሱ ሊያድናችሁ ከቶ አይችልም!


ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ከከተማችሁ ወጥታችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ አዞአችኋል፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁም እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላና የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤


“የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሆይ፥ የምትታመንበት አምላክ ‘ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አትወድቅም’ ብሎ አያታልህ፤


የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው።


ኢሳይያስ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብላችሁ ለጌታችሁ ንገሩት አላቸው፤ ‘የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች ሲሰድቡኝ ስለ ሰማችሁት ቃል አትፍሩአቸው።


እግዚአብሔር ከለላዬ ነው፤ እንዴት “እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ሽሽ” ትሉኛላችሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ጋሻዬ ነህ፤ ድልን በማጐናጸፍ ክብርን የምትሰጠኝ አንተ ነህ።


እናንተ ሰዎች፥ እስከ መቼ ክብሬን ታዋርዳላችሁ? እስከ መቼስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? እስከ መቼስ ሐሰትን ትፈልጋላችሁ?


እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤ በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ ልቤ በሐዘን ይሰበራል።


“እግዚአብሔር ትቶታል፤ ተከታትለን እንያዘው፤ የሚያድነው ማንም የለም” ይላሉ።


አሁንም በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ደካማ በምሆንበትም ጊዜ አትተወኝ።


እርሱ በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሎአል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው!”


ሕዝቡ ቆሞ ይመለከት ነበር፤ የአይሁድ አለቆችም “ሌሎችንስ አዳነ እንግዲህ እርሱ የተመረጠው የእግዚአብሔር መሲሕ ከሆነ እስቲ ራሱን ያድን!” እያሉ ያፌዙበት ነበር።


跟着我们:

广告


广告