Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 15:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና፥ የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በይሁዳ ላይ አደጋ እንዲጥሉባት የላካቸው ይኸው ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠበት ዘመን ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔን ይሁዳን እንዲወጉ አደረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና፥ የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በይሁዳ ላይ አደጋ እንዲጥሉባት የላካቸው ይኸው ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠበት ዘመን ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 በዚ​ያም ወራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሶ​ር​ያን ንጉሥ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ፋቁ​ሔን በይ​ሁዳ ላይ መላክ ጀመረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 በዚያም ወራት እግዚአብሔር የሶርያን ንጉሥ ረአሶንንና የሮሜልዩን ልጅ ፋቁሔን በይሁዳ ላይ መስደድ ጀመረ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 15:37
18 交叉引用  

በዚያም ዘመን እግዚአብሔር የእስራኤል ግዛት ስፋቱ እንዲቀነስ ማድረግ ጀመረ፤ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤልን ድል ነሥቶ የእስራኤልን ግዛት ሁሉ ያዘ።


ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በኀምሳ ሁለተኛው ዓመት የረማልያ ልጅ ፈቁሔ በእስራኤል ነገሠ፤ መኖርያውንም በሰማርያ አድርጎ ኻያ ዓመት ገዛ።


ኢዮአታም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።


ኢዮአታም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አካዝ ነገሠ።


የሶርያ ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ በመጣል ከበቡአት፤ ነገር ግን አካዝን ድል ሊያደርጉት አልቻሉም።


የጥፋት መልእክተኞች ቡድን የሆኑትን አስፈሪውንና ኀይለኛ ቊጣውን፥ ማዋረዱንና ማስጨነቁን ላከባቸው።


ከዖዝያን ልጅ ከኢዮአታም የተወለደው አካዝ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን፥ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የረማልያ ልጅ ፋቁሔ ጦርነት ማስነሣት ፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ነገር ግን ኢየሩሳሌምን ድል ሊያደርጉአት አልቻሉም።


ስለምን ቢባል፥ የሶርያ ራስ ደማስቆ ስትሆን፥ የደማስቆም ራስ ረጺን ነው፤ ስለ እስራኤልም የሆነ እንደ ሆነ፥ በስልሳ አምስት ዓመቶች ጊዜ ውስጥ ብትንትናቸው ወጥቶ በመንግሥትነት መታወቃቸው ይቀራል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ሕዝብ እንደ ዓሣ የሚያጠምዱና እንደ አውሬ የሚያድኑ ብዙ ሰዎችን እልካለሁ፤ በየተራራውና በየኰረብታው በቋጥኞች ውስጥ ባሉ ዋሻዎችም እያደኑ ይይዙአቸዋል።


እነሆ፥ ጥፋትን የስሜ መጠሪያ በሆነችው ከተማ እጀምራለሁ፤ ታዲያ ከቅጣት የሚያመልጡ ይመስላቸዋልን? እኔ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ጦርነትን ስለማመጣ ከቶ ከቅጣት የሚያመልጡ የሉም፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።


ከዚያም የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አገልጋዬ የሆነውን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ወደዚህ ስፍራ አምጥቼ አንተ በቀበርካቸው በእነዚያ ድንጋዮች ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ የቤተ መንግሥት ድንኳኖቹን የሚተክልባቸው መሆኑን ንገራቸው።


ይህ ሁሉ መሆን በሚጀምርበት ጊዜ መዳናችሁ ቀርቦአልና ቀና ብላችሁ ወደ ላይ ተመልከቱ።”


ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ለሚልካቸው ለጠላቶችህ አገልጋይ ትሆናለህ። በሁሉ ነገር በመቸገርም ትራባለህ፤ ትጠማለህ፤ ትታረዛለህ። ፈጽሞ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር አንተን በጠላቶችህ እንደ ብረት በጠነከረ የአገዛዝ ቀንበር በብርቱ እንድትጨቈን ያደርጋል።


በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤


跟着我们:

广告


广告