Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 13:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ኤልሳዕ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም “ፍላጻውን አስፈንጥር!” አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፥ “ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ቀጥሎም፣ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለው፤ ከፈተውም፤ ኤልሳዕም፣ “በል አስፈንጥረው” አለው፤ አስፈነጠረውም፤ ከዚያም፣ “የእግዚአብሔር የድል ቀስት! ሶርያ ድል የምትሆንበት ቀስት!” አለ። ኤልሳዕም እንደ ገና “ሶርያውያንንም አፌቅ ላይ ፈጽመህ ድል ታደርጋቸዋለህ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ኤልሳዕ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም “ፍላጻውን አስፈንጥር!” አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፥ “ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “የም​ሥ​ራ​ቁ​ንም መስ​ኮት ክፈት” አለ፤ ከፈ​ተ​ውም። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ወር​ውር” አለው፤ ወረ​ወ​ረ​ውም እር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒት ፍላጻ ነው፤ ከሶ​ርያ የመ​ዳን ፍላጻ ነው፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ ሶር​ያ​ው​ያ​ንን በአ​ፌቅ ትመ​ታ​ለህ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 “የምሥራቁን መስኮት ክፈት፤” አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም “ወርውር!” አለ፤ ወረወረውም። እርሱም “የእግዚአብሔር መድኃኒት ፍላጻ ነው፤ በሶርያ ላይ የመድኃኒት ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ሶርያውያንን በአፌቅ ትመታለህ፤” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 13:17
14 交叉引用  

በሾላ ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመምታት የወጣ መሆኑን ዐውቀህ ፈጥነህ አጥቃ።”


ስለዚህም በተከታዩ የጸደይ ወቅት ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ በእስራኤል ላይ አደጋ ለመጣል ወደ አፌቅ ከተማ ገሠገሠ፤


ሶርያውያንና እስራኤላውያን ፊት ለፊት ተፋጠው በየጦር ሰፈራቸው እስከ ሰባት ቀን ቈዩ፤ በሰባተኛውም ቀን ጦርነት ጀምረው በዚያኑ ቀን እስራኤላውያን አንድ መቶ ሺህ የሶርያውያንን እግረኛ ጦር ወታደሮችን ገደሉ።


ኤልሳዕም “ፍላጻዎቹን ለማስፈንጠር ተዘጋጅ” አለው፤ ንጉሡም እንደታዘዘው አደረገ፤ ኤልሳዕም እጆቹን በንጉሡ እጆች ላይ አኖረ።


ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ንጉሡን “ሌሎቹንም ፍላጻዎች አንሥተህ በእነርሱ ምድርን ምታ!” አለው። ንጉሡም ምድርን ሦስት ጊዜ መትቶ አቆመ፤


ተአምራት የምታሳይበትንም ይህን በትር ይዘህ ሂድ።”


እግዚአብሔርም “በእጅህ የያዝከው ምንድን ነው?” አለው። እርሱም “በትር ነው” አለ።


የመስቀሉ ነገር ለሚጠፉት ሰዎች እንደ ሞኝነት ይቈጠራል፤ ለምንድን ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው።


አፌቅ፥ ላሻሮን፥


እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ ስለዚህም እስራኤላውያን አቤንዔዜር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም አፌቅ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤


跟着我们:

广告


广告