2 ቆሮንቶስ 8:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ብዙ ጊዜ በብዙ መንገድ ተፈትኖ ትጉህ ሆኖ የተገኘውን ወንድማችንን ከነቲቶ ጋር የላክነውም በዚሁ ምክንያት ነው፤ እርሱ በእናንተ ላይ ያለው እምነት ትልቅ ስለ ሆነ አሁን በዚህ ሥራ ለመርዳት ያለው ትጋት ከምንጊዜውም የበለጠ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ደግሞም ብዙ ጊዜ በብዙ መንገድ ተፈትኖ ትጉ ሆኖ የተገኘውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋራ ልከነዋል፤ አሁንም በእናንተ እጅግ ከመታመኑ የተነሣ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እየተጋ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በብዙ ነገር ተፈትኖና በብዙ ጉዳዮች ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር ልከነዋል። አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከበፊት ይልቅ እጅግ ትጉህ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 በብዙ የፈተንነውንና በሁሉም ነገር ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ብዙ ጊዜም በብዙ ነገር መርምረን ትጉ እንደ ሆነ ያገኘነውን፥ አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን። 参见章节 |