Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እኛ የምንኖረውም ጌታን በማመን እንጂ እርሱን በማየት አይደለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በእ​ም​ነት እን​ኖ​ራ​ለን፤ በማ​የ​ትም አይ​ደ​ለም።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 5:7
10 交叉引用  

አሁን በመስተዋት እንደምናየው ዐይነት በድንግዝግዝ እናያለን፤ በዚያን ጊዜ ግን በግልጥ እናያለን፤ አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እግዚአብሔር እኔን የሚያውቀኝን ያኽል ሙሉ ዕውቀት ይኖረኛል።


እናንተ በእምነታችሁ የጸናችሁ ስለ ሆናችሁ እናንተን ደስ እንዲላችሁ አብረናችሁ እንሠራለን እንጂ በእምነታችሁስ አናዛችሁም።


እኛ የምንጠብቀው የማይታየውን ነገር እንጂ የሚታየውን አይደለም፤ የሚታየው ነገር ጊዜያዊ ነው፤ የማይታየው ግን ዘለዓለማዊ ነው።


እኔ ከክርስቶስ ጋር እንደ ተሰቀልኩ ያኽል ስለምቈጥር ከእንግዲህ ወዲህ ክርስቶስ በእኔ ውስጥ ይኖራል እንጂ እኔ ለራሴ ሕይወት የምኖር አይደለሁም፤ አሁንም በሥጋዊ አካሌ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ በማመን በተገኘው ሕይወት ነው።


እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁና በሰላም ዕረፍት አድርጋችሁ ወደምትኖሩባት ርስት ገና አልገባችሁም፤


የእኔ የሆነ ጻድቁ ሰው ግን በእምነት ሕይወትን ያገኛል፤ ወደ ኋላው ቢያፈገፍግ ግን እኔ በእርሱ አልደሰትም።”


ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።


በዓለም ሁሉ ያሉ ወንድሞቻችሁ ይህን ዐይነት መከራ እንደሚቀበሉ በማወቅ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።


跟着我们:

广告


广告