Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ጠላቶች ያሳድዱናል፤ ግን ወዳጆች አጥተን አናውቅም፤ ተመተን እንወድቃለን፤ ግን አንሞትም፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ብንሰደድም ተጥለን አንቀርም፤ መትተው ቢጥሉንም አንጠፋም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እንሰደዳለን እንጂ አንተውም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እን​ሰ​ደ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጣ​ልም፤ እን​ወ​ድ​ቃ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጠ​ፋም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 4:9
19 交叉引用  

እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳል፤ ትሑታንን ግን ያድናቸዋል።


“ከወጣትነቴ ጀምሮ ጠላቶቼ በጭካኔ አሳደዱኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።


አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውከኝ? እኔን ከማዳን የራቅኸው ለምንድን ነው? ከመቃተት ድምፄስ የራቅኸው ለምንድን ነው?


እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድን ይወዳል፤ ታማኞቹንም አይተዋቸውም፤ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል፤ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ? ለምንስ እጨነቃለሁ። በእግዚአብሔር እተማመናለሁ ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።


እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ፤ ለምንስ እጨነቃለሁ። በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።


አምላክ ሆይ! በአንተ የሚተማመኑትን ሁሉ ስለማትተዋቸው ስምህን የሚያውቁ ሁሉ ይተማመኑብሃል።


ጻድቅ ሰው ሰባት ጊዜ ቢወድቅ እንኳ እንደ ገና ይነሣል፤ ዐመፀኞች ግን ጥፋት ይደርስባቸዋል።


በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።


ከእንግዲህ ወዲህ “የተተወች” ተብለሽ አትጠሪም፤ ምድርሽም “ባድማ” ተብላ አትጠራም። የምትጠሪበትም አዲስ ስም፥ “እግዚአብሔር በእርስዋ ደስ ይለዋል!” የሚል ይሆናል፤ ምድርሽም “ባለ ባል” ተብላ ትጠራለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባል እንዳላት ሴት ትሆናለች።


ጠላቴ ሆይ! እኔ ብወድቅም እንኳ እንደገና እነሣለሁና በእኔ ደስ አይበልህ፤ አሁን በጨለማ ውስጥ ብሆንም እግዚአብሔር ያበራልኛል።


ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥


አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን አስታውሱ፤ እኔን ካሳደዱኝ እናንተንም ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ከጠበቁ ቃላችሁንም ይጠብቃሉ።


ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማነው? ችግር ወይስ መከራ? ስደት፥ ወይስ ራብ? ወይስ ራቊትነት፥ ወይስ አደጋ? ወይስ ሰይፍ?


ነገር ግን የተዋረዱትን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን።


የኢየሱስ ክርስቶስ ወገኖች ሆነው መንፈሳዊ ሕይወትን መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ስደት ይገጥማቸዋል።


ከገንዘብ ፍቅር ራቁ፤ ያላችሁ ይብቃችሁ፤ እግዚአብሔር “ከቶ አልጥልህም፤ ፈጽሞም አልተውህም” ብሎአል።


跟着我们:

广告


广告