2 ቆሮንቶስ 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 አገልግሎታችንን መፈጸም እንድንችል ብቁ የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው እንጂ እኛስ በገዛ ራሳችን ምንም ለማድረግ ብቁ አይደለንም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፣ በራሳችን ብቃት ከእኛ ነው የምንለው አንዳች ነገር የለንም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን የሚሆን አንዳችን ነገር ልናስብ እኛ የበቃን አይደለንም፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ኀይላችን ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ ከእኛ ከራሳችን እንደ ሆነ አድርገን ምንም ልናስብ አይገባንም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤ 参见章节 |