Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 12:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ታዲያ፥ እኔ እውነት ስለምናገር መመካት ብፈልግም ሞኝ አልሆንም፤ ነገር ግን ማንም በእኔ ላይ ከሚያየውና ከእኔ ከሚሰማው በላይ ግምት እንዳይሰጥ ብዬ ከመመካት እቈጠባለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መመካት ብፈልግ እንኳ እንደ ሞኝ መቈጠር የለብኝም፤ ምክንያቱም የምናገረው እውነት ነው። ነገር ግን ማንም ስለ እኔ ከሚያየውና ከሚሰማው በላይ እንዳይገምተኝ ከመመካት እቈጠባለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ልመካ ብፈልግ አልሞኝም፤ ምክንያቱም የምናገረው እውነት ነው፤ ነገር ግን ማንም ስለ እኔ ከሚያየውና ከሚሰማው ባለፈ የበለጥኩ አድርጎ እንዳያስበኝ ይህን ከመናገር እቆጠባለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ልመካ ብሻም አላ​ዋቂ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እው​ነ​ቱን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ስላ​ዩ​ኝና ስለ ሰሙኝ እን​ደ​ም​በ​ልጥ አድ​ር​ገው እን​ዳ​ይ​ጠ​ራ​ጠ​ሩኝ ትቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ልመካ ብወድስ ሞኝ አልሆንም፥ እውነትን እላለሁና፤ ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 12:6
12 交叉引用  

እንደዚህ አይደለም ከተባለ እኔ ሀሰተኛ መሆኔንና የተናገርኩትም ቃል ትክክል አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ማነው?”


በክርስቶስ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ኅሊናዬም እንደማልዋሽ ይመሰክርልኛል።


ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? እነርሱ እናንተ እንድታምኑ ያደረጉአችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ እያንዳንዳቸው የሚያገለግሉትም ጌታ ለያንዳንዳቸው በመደበላቸው ሥራ ነው፤


እግዚአብሔር ታማኝ ስለ ሆነ እኛም የምንነግራችሁ “አዎን ወይም አይደለም” የሚል የማወላወል ቃል አይደለም።


“ማንም ሰው እኔ ሞኝ የሆንኩ አይምሰለው” ብዬ እንደገና እናገራለሁ። ሞኝ ብመስላችሁም እንኳ ጥቂት እንድመካ እንደ ሞኝ አድርጋችሁ ቊጠሩኝ።


ለዘለዓለም የተመሰገነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር እንደማልዋሽ ያውቃል።


እንደ ሞኝ ተናገርኩ! ታዲያ፥ እንዲህ እንድናገር ያደረጋችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እኔን ማመስገን የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ፤ እኔ ማንነቴ ያልታወቀ ሰው ብሆንም እንኳ ታላላቅ ከተባሉት ሐዋርያት በምንም አላንስም።


ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል።


እብዶች ብንሆን ለእግዚአብሔር ስንል ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆንም ለእናንተ ስንል ነው።


በእናንተ የነበረኝን ትምክሕት ለቲቶ ነግሬው ነበር፤ እናንተም አላሳፈራችሁኝም፤ ሁልጊዜ እውነትን እንነግራችሁ ነበር፤ ይህም ስለ እናንተ ለቲቶ የነገርነው ትምክሕት እውነት በመሆኑ ተረጋግጦአል።


跟着我们:

广告


广告