2 ዜና መዋዕል 7:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እስራኤላውያን እሳት ከሰማይ ሲወርድና የእግዚአብሔርም ክብር በቤተ መቅደስ ላይ ማረፉን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው፦ “እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነው!” እያሉ ሰገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እስራኤላውያንም ሁሉ እሳቱ ሲወርድ፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ከቤተ መቅደሱ በላይ ሲያዩ፣ በመተላለፊያው ወለል ላይ ተንበረከኩ፤ በግንባራቸውም ወደ መሬት ተደፍተው ሰገዱ፤ እንዲህ እያሉም ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረቡ፤ “እርሱ ቸር ነውና፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉም እግዚአብሔርን አመሰገኑ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የጌታም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ እንዲህም ብለው ጌታን አመሰገኑ፦ “እርሱ መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድንጋይ በተነጠፈበትም ምድር በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ “እርሱ መልካም ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና” ብለውም እግዚአብሔርን አመሰገኑ። 参见章节 |