Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 7:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ይህ ቤተ መቅደስ እነሆ አሁን ከፍ ያለ ክብር አለው፤ በዚያን ጊዜ ግን በቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚያልፍ ሰው ሁሉ በመገረም ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ ስለምን እንደዚህ አደረገ?’ ብሎ ይጠይቃል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ይህ ቤተ መቅደስ አሁን እጅግ የሚያስደንቅ ቢሆንም በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያደረገው ስለ ምን ይሆን?’ ይላል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያዩ በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ፦ ‘ጌታ በዚህ አገርና በዚህ ቤት ለምን እንዲህ አደረገ?’ ብለው ይደነቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከፍ ከፍ ብሎ የነ​በ​ረ​ው​ንም ይህን ቤት እያየ በዚያ የሚ​ያ​ልፍ መን​ገ​ደኛ ሁሉ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሀገ​ርና በዚህ ቤት ስለ ምን እን​ዲህ አደ​ረገ?’ ብሎ ይደ​ነ​ቃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያዩ በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ ‘እግዚአብሔር በዚህ አገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ?’ ብለው ይደነቃሉ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 7:21
12 交叉引用  

በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ፤ እናንተም እንደምታዩት በእነርሱ ላይ ፍርሀትንና ድንጋጤን አምጥቶባቸዋል፤ መዘባበቻም አድርጎአቸዋል።


ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ለምንድነው? “ልብሴስ ተቀዶ የተደፈርኩት ስለምንድነው?” ብለሽ ብትጠይቂ፤ ይህ ሁሉ የደረሰብሽ ኃጢአትሽ እጅግ የከፋ በመሆኑ ምክንያት እንደ ሆነ ዕወቂ።


ይህችን ከተማ የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነግጣል፤ በደረሰባት ችግርም ይገረማል።


እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ንጉሥ ኢኮንያን ከተጣለ በኋላ ማንም እንደማይፈልገው ሰባራ ገንቦ መሆኑ ነውን? እርሱና ልጆቹ ተማርከው ወደማያውቁት አገር የተወሰዱት ለምንድን ነው?”


ትእዛዜን የማትፈጽሙ ከሆነ ግን ይህ ቤተ መቅደስ ፈራርሶ እንደሚወድቅ በራሴ በመማል አረጋግጥላችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤዶም የምታስደነግጥ ትሆናለች፤ በዚያ በኩል ሲያልፍ የሚያያት ሁሉ ይደነግጣል፤ በደረሰባት ጥፋትም ይገረማል።


ኤርምያስ ሆይ! ሕዝቡ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ነገር ያደረሰብን ስለምድን ነው?’ ብለው በጠየቁህ ጊዜ ከእኔ ተለይተው በገዛ ምድራቸው ላይ ባዕዳን አማልክትን እንዳመለኩ ሁሉ፥ እነርሱም ራሳቸው የእነርሱ ባልሆነ አገር የባዕድ ሕዝብ አገልጋዮች መሆናቸው እንደማይቀር ንገራቸው።”


ከቊጣዬ የተነሣ በባቢሎን መኖር የሚችል የለም፤ ፈራርሳ ትቀራለች፤ በአጠገብዋ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ ይደነግጣልም።


跟着我们:

广告


广告