Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ፥ ወይም ሰብሉን እንዲበላ አንበጣ በምልክበት ጊዜ፥ ወይም ቸነፈር በሕዝቤ ላይ በማወርድበት ጊዜ ሁሉ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣ በማዝዝበት ጊዜ፣ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር በምሰድድበት ጊዜ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዝናብ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ሰማ​ያ​ቱን ብዘጋ፥ ወይም የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን እን​ጨት ሁሉ ይበላ ዘንድ አን​በ​ጣን ባዝ​ዘው፥ ወይም በሕ​ዝቤ ላይ ቸነ​ፈር ብሰ​ድድ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን ይበላ ዘንድ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝብ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 7:13
17 交叉引用  

እግዚአብሔር መጥቶ ቢያስር፥ ወደ ፍርድ ሸንጎም ቢያቀርብ፥ ማን ይከለክለዋል?


እግዚአብሔር ያፈረሰውን ማንም መልሶ መሥራት አይችልም፤ እግዚአብሔር ያሰረውንም ማንም ሊፈታው አይችልም፤


እርሱ ባዘዘው መሠረት ሊቈጠር የማይችል የአንበጣና የኲብኲባ መንጋ መጣ።


እዚያ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን አገር እንደ ጨው ምድር የማታፈራ አደረጋት።


ለዘመናት እንደ ትልቅ ሠራዊት የላክሁባችሁ እንደ ውሽንፍር የሚገርፉ አንበጦች፥ ኲብኲባዎች፥ ተምቾችና የሚርመሰመሱ አንበጦች የፈጁባችሁን ሰብል እተካላችኋለሁ።


አዝመራችሁ ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ እንዲቋረጥ አደረግሁ፤ በአንድ ከተማ ሲዘንብ በሌላው ከተማ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ ለአንዱ እርሻ ሲዘንብለት ሌላው እርሻ ዝናብ አጥቶ ደረቀ።


እነሆ፥ እኔ ቸነፈር አምጥቼ በመቅሠፍት እደመስሳቸዋለሁ፤ አንተን ግን ከእነርሱ ይበልጥ ታላቅና ብርቱ ለሆነ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።”


“ስሙኝ እውነቱን ልንገራችሁ፤ በነቢዩ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ዝናም ባለመዝነቡ በአገሩ ሁሉ ብርቱ ራብ ሆኖ ነበር፤ በዚያን ጊዜ በእስራኤል አገር ብዙ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ነበሩ።


ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይቈጣል፤ ሰማያትን ዘግቶ ምድሪቱን ዝናብ እንዳይዘንብባትና ፍሬ እንዳትሰጥ ያደርጋል፤ እናንተም እግዚአብሔር ከሚሰጣችሁ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።


እነርሱ ትንቢት በሚናገሩባቸው በእነዚህ ቀኖች ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ለመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ እንዲሁም ውሃዎችን ወደ ደም ለመለወጥና በሚፈልጉትም ጊዜ ሁሉ በማንኛውም ዐይነት መቅሠፍት ምድርን ለመምታት ሥልጣን አላቸው።


“ለፊላደልፍያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ቅዱስና እውነተኛ ከሆነው፥ የዳዊት ቤት ቊልፍ ከያዘው የተነገረ ነው፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋውም፤ እርሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍተውም።


跟着我们:

广告


广告