Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12-13 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ሕዝቡ ባለበት በመሠዊያው ፊት ለፊት፥ በአደባባዩ መካከል በሚገኘው መድረክ ላይ ወጥቶ ቆመ። ስፋቱና ርዝመቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሴንቲ ሜትር፥ ቁመቱ አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር የሆነ መድረክ ከነሐስ አሠርቶ በአደባባዩ መካከል ተክሎት ነበር፤ እርሱም ሕዝቡ ሁሉ ሊያዩት በሚችሉበት በዚህ መድረክ ላይ በመንበርከክ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ እንዲህ ሲል ጸለየ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ ባለበት በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት እጆቹን ዘርግቶ ቆመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰሎሞንም የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ እያዩት በጌታ መሠዊያ ፊት ቆሞ እጆቹን ዘረጋ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ ፊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አን​ጻር ቆሞ እጆ​ቹን ዘረጋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12-13 ሰሎሞንም ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መደገፊያ ሠርቶ በአደባባዩ መካከል ተክሎት ነበር፤ በላዩም ቆመ፤ በእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ፊት በጕልበቱ ተንበርክኮ እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ እያዩ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ቆሞ እጆቹንም ዘርግቶ እንዲህ አለ

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 6:12
15 交叉引用  

እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየችው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ “ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው! ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።


ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሓሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።


እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦትም በቤተ መቅደሱ ውስጥ አኑሬአለሁ።”


“ሆኖም፥ ልብህን የቀና ብታደርግ እጅህንም ዘርግተህ ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ፥


ጸሎቴን እንደ ዕጣን፥ የተዘረጉትን እጆቼን እንደ ማታ መሥዋዕት አድርገህ ተቀበል።


እጆቼን ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤ ደረቅ ምድር ውሃ እንደሚያስፈልገው እንዲሁም ነፍሴ አንተን ተጠማች።


ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እጄን አንሥቼ ለእርዳታ በምጮኽበት ጊዜ እባክህ ጸሎቴን ስማኝ።


በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤ ለጸሎትም እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ።


መልክተኞች ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያም እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።


ሙሴ ከንጉሡ ፊት በመውጣት ከከተማው ውጪ ሄደ፤ እጁንም ዘርግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ዝናቡም በአንድ ጊዜ ቆመ።


ከእናንተ መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራና ለአገልጋዩ ቃል የሚታዘዝ ማነው? ብርሃን የሌለው በጨለማ የሚመላለስ በእግዚአብሔር ይታመን፤ እምነቱንም በአምላኩ ላይ ይጣል።


እንግዲህ በየስፍራው ያሉ ወንዶች ቊጣንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ።


跟着我们:

广告


广告