2 ዜና መዋዕል 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እንዲሁም ዐሥር ጠረጴዛዎችን አሠርቶ በቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል ውስጥ አምስቱን በሰሜን፥ አምስቱን በደቡብ በኩል አኖራቸው፤ በተጨማሪም አንድ መቶ ማንቈርቈሪያዎችን ከወርቅ አሠራ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ዐሥር ጠረጴዛ ሠርቶም ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት ዐምስቱን በስተ ደቡብ፣ ዐምስቱን ደግሞ በስተሰሜን በኩል አኖራቸው፤ ደግሞም አንድ መቶ ጐድጓዳ የወርቅ ሳሕኖች ሠራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 አሥሩንም ገበታዎች ሠርቶ አምስቱን በቀኝ አምስቱን በግራ በመቅደስ ውስጥ አኖራቸው። አንድ መቶም የወርቅ ድስቶች ሠራ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ዐሥሩንም የወርቅ ገበታዎች ሠርቶ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ በመቅደሱ ውስጥ አኖራቸው። አንድ መቶም የወርቅ ጽዋዎችን ሠራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ዐሥሩንም ገበታዎች ሠርቶ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱን በግራ በመቅደስ ውስጥ አኖራቸው። አንድ መቶም የወርቅ ድስቶች ሠራ። 参见章节 |