Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የገንዳው የውጪው ክፈፍ ዙሪያው በሙሉ አንዱ በሌላው ላይ የተነባበረ ሆኖ በሁለት ረድፍ የተሠሩ ጌጦች ነበሩት፤ እነዚህም ጌጦች በሙሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በበሬዎች ቅርጽ የተሠሩ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከገንዳው ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኰርማ ቅርጾች ነበሩበት፤ ኰርማዎቹም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በበታቹም ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድም ክንድ ዐሥር፥ እንደ በሬዎች ያሉ ቅርጾች በኩረው ላይ አዞረበት፤ ኩሬውንም በቀለጠ ጊዜ የበሬዎቹም ቅርጾች በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በበ​ታ​ች​ዋም፥ በዙ​ሪ​ያዋ በዐ​ሥሩ ክንድ የበ​ሬ​ዎች ምስ​ሎች ነበሩ። ኵሬ​ዋ​ንም ይከ​ብ​ቡ​አት ነበር። በሬ​ዎ​ቹም በሁ​ለት ተራ ሁነው ከኵ​ሬው ጋር በአ​ን​ድ​ነት ቀል​ጠው የተ​ሠሩ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በበታቹም ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድም ክንድ አሥር፥ ጕብጕቦች አዞረበት፤ ኵሬውም በቀለጠ ጊዜ ጕብጕቦቹ በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 4:3
8 交叉引用  

እንዲሁም ጥልቀቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ አጋማሽ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር፥ ዙሪያው ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የሆነ ክብ ገንዳ አሠራ፤


በርሜሉም ከነሐስ በተሠሩና ፊታቸውን ወደ ውጪ ባዞሩ በዐሥራ ሁለት የበሬዎች ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ የኰርማዎቹ ምስሎችም ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ፥ ሦስቱ ደግሞ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ነበሩ።


እያንዳንዱ ፍጥረት አራት የተለያዩ ፊቶች ነበሩት፤ ይኸውም ከፊት ለፊት የሰው መልክ የሚመስል፥ በስተቀኝ በኩል የአንበሳ መልክ፥ በስተግራ የበሬ ፊት፥ በስተ ኋላም የንስር መልክ የሚመስል ነበሩት።


እያንዳንዱ ኪሩብ አራት ፊቶች ነበሩት፤ የመጀመሪያው የበሬ ፊት፥ ሁለተኛው የሰው፥ ሦስተኛው የአንበሳ፥ አራተኛው ደግሞ የንስር ፊት ይመስል ነበር።


አንተና ወታደሮችህ እስከ ስድስት ቀን ድረስ በቀን አንድ ጊዜ የከተማይቱን ቅጽር በሰልፍ ትዞሩአታላችሁ።


የመጀመሪያው እንስሳ አንበሳ ይመስል ነበር፤ ሁለተኛው በሬ ይመስል ነበር፤ ሦስተኛው የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛው የሚበር ንስር ይመስል ነበር።


跟着我们:

广告


广告