Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 36:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ኢዮአቄም በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እርሱም ኃጢአት በመሥራቱ አምላኩን እግዚአብሔርን አሳዘነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ። በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ኢዮ​አ​ቄ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ዘካራ የም​ት​ባል የኔ​ሬ​ያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበ​ረች፤ አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ። 5 ‘ሀ’ በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ​ዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት። ከእ​ር​ሱም ከዳ። 5 ‘ለ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንና የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንና የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ንን ልጆ​ችና የሰ​ማ​ር​ያን አደጋ ጣዮች ላከ​በት፤ ከዚ​ህም በኋላ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ በነ​ቢ​ያት እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ራቁ። 5 ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለ​ሠ​ራ​ቸው ኀጢ​አ​ቶ​ችና ኢዮ​አ​ቄም ስላ​ፈ​ሰ​ሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ነበር። 5 ‘መ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው አል​ፈ​ለ​ገም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 36:5
11 交叉引用  

እንዲሁም የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠበት ዘመንና፥ ከዚያም በኋላ የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ነግሦ ዐሥራ አንድ ዓመት እስከሆነው ድረስ ማለት በዚያው ዓመት በአምስተኛው ወር የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ተወሰደ ድረስ የእግዚአብሔር ቃል በኤርምያስ አማካይነት ተነግሮአል።


የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ እንደ ነገሠ ወዲያውኑ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቆመህ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለስግደት ወደዚያ ለሚመጡት ሕዝብ እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ አንድ ነገር እንኳ ሳታስቀር ንገራቸው።


የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦


የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤


የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ባሮክ በቃል የነገርኩትን ሁሉ በብራና ጥቅል ጻፈው፤


ኢዮአቄም በይሁዳ ላይ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት።


እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ።


跟着我们:

广告


广告