Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 35:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ወገኖቻችሁ የሆኑ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ ይከተሉ ዘንድ ራሳችሁን አንጽታችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም የፋሲካውን በጎች ዕረዱ፤ ራሳችሁን ቀድሱ፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘውም መሠረት ዕርዶቹን ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፋሲካውንም እረዱ፥ እናንተም ተቀደሱ፥ ጌታም በሙሴ አንደበት የተናገረውን ቃል እንዲያደርጉ ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ እረዱ፤ እና​ን​ተም ተቀ​ደሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታደ​ርጉ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ አዘ​ጋጁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እናንተም ተቀደሱ፤ እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ የተናገረውን ቃል ያደርጉ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።”

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 35:6
21 交叉引用  

ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ንጹሕ ልብስም ልበሱ፤


ሌዋውያኑንም እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እናንተ ለሌዋውያን ጐሣዎች መሪዎች ናችሁ፤ የእስራኤል አምላክን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት እኔ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ ተሸክማችሁ ታመጡ ዘንድ ራሳችሁንና ሌዋውያን ወገኖቻችሁን ሁሉ ቀድሱ፤


እነዚህም ሰዎች ሌዋውያን ወገኖቻቸውን ሰብስበው ሁሉም በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ራሳቸውን አነጹ፤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ እንዳዘዛቸው ሌዋውያኑ በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ቤተ መቅደሱን አነጹ፤


ይህን ሁሉ እንስሳ ዐርደው ቆዳውን ለመግፈፍ በቂ ካህናት ስላልነበሩ ሥራው እስኪጠናቀቅና የነጹ ካህናት እስከሚገኙ ድረስ ሌዋውያን ይረዱአቸው ነበር፤ በመንጻት ረገድ ከካህናት ይልቅ ሌዋውያን ዘወትር ዝግጁዎች ነበሩ።


እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ሌዋውያን! ራሳችሁን መቀደስና የቀድሞ አባቶቻችሁን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቀደስ ማንጻት አለባችሁ፤ ቤተ መቅደሱን የሚያረክስ ነገር ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ማስወገድ ይኖርባችኋል።


ንጉሥ ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ክብር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ሕዝቡ የፋሲካን በግ ዐረደ፤


ለፋሲካውም በዓል የታረዱትን የበግና የፍየል ጠቦቶች ሌዋውያኑ ቆዳቸውን ገፈፉአቸው፤ ካህናቱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩ፤


ንጉሥ ኢዮስያስ በዚያው በፋሲካ በዓል የተገኙ ሰዎች መሥዋዕት አድርገው የሚያቀርቡአቸውን የራሱ ሀብት ከሆኑ የቀንድ ከብቶች፥ እንዲሁም የበግና የፍየል መንጋ፥ ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶችንና ሦስት ሺህ ወይፈኖችን ሰጠ፤


እዚያ የነበሩት ካህናት ሁሉ የአገልግሎት ምድባቸውን ሳይመለከቱ በአንድነት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጥተው ነበር፤


የግብዣዎቹ ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ኢዮብ በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹን ያስጠራና በእያንዳንዱ ልጁ ስም መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ይህንንም የሚያደርገው “ምናልባት ከልጆቼ አንዱ እግዚአብሔርን በመስደብ በድሎ ይሆናል!” በሚል ስጋት ልጆቹን ከኃጢአት ለማንጻት ነበር። ኢዮብ ይህን ሥርዓት ሳያቋርጥ ዘወትር ይፈጽም ነበር።


በሂሶጵ ቅጠል ረጭተህ ኃጢአቴን አስወግድልኝ፤ እኔም እነጻለሁ። እጠበኝ፤ እኔም ከበረዶ ይበልጥ ነጭ እሆናለሁ።


እነዚህንም እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ጠብቁአቸው። በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ የእስራኤል ኅብረተሰብ ሁሉ እንስሶቹን ይረዱ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፥ “ወደ ሰዎቹ ሂድ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ አድርገህ ታቀርባቸው ዘንድ ዛሬና ነገ ሰውነታቸውን እንዲያነጹና ልብሳቸውንም እንዲያጥቡ ንገራቸው፤


ሙሴም ሰዎቹን “ለተነገወዲያው ዕለት ተዘጋጁ፤ እስከዚያም ቀን ድረስ ወደ ሴት አትቅረቡ” አላቸው።


ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት ሰብስባችሁ፥ ለተቀደሰ ጉባኤ አዘጋጁ፤ ሽማግሌዎችን ጥሩ፤ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን ጭምር ሰብስቡ፤ ሙሽራዎችም ሳይቀሩ ከጫጒላቸው ይውጡ።


跟着我们:

广告


广告