Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 35:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እንዲሁም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለለዩ፥ የመላው እስራኤል መምህራን ለሆኑ ሌዋውያን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ “የተቀደሰውን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑሩት፤ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ማገልገል እንጂ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት በትከሻችሁ ተሸክማችሁ ከስፍራ ወደ ስፍራ መውሰድ የለባችሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እስራኤልን ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩትና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አላቸው፤ “የእግዚአብሔርን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ አኑሩ፤ በእናንተ ትከሻ አትሸከሙት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለጌታም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን ጌታንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መሥ​ራት የሚ​ች​ሉ​ትን ሌዋ​ው​ያን ራሳ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ያ​ነ​ጹና ቅድ​ስ​ቲ​ቱ​ንም ታቦት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞን በሠ​ራው ቤት ውስጥ እን​ዲ​ያ​ኖሩ አዘ​ዛ​ቸው። ንጉ​ሡም ኢዮ​ስ​ያስ አለ፥ “በት​ከ​ሻ​ችሁ የም​ት​ሸ​ከ​ሙት አን​ዳች ነገር አይ​ኑር፤ አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሕዝ​ቡን እስ​ራ​ኤ​ልን አገ​ል​ግሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 35:3
15 交叉引用  

ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ሌዋውያን መሸከም አይኖርባቸውም።”


ኢዮሣፍጥ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ቤንሐይል፥ አብድዩ፥ ዘካርያስ፥ ናትናኤልና ሚክያስ ተብለው የሚጠሩትን ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖች በይሁዳ ከተሞች እንዲያስተምሩ ላካቸው።


ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር የተደረገውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በመምራት ከፍ ያለ ችሎታ ስላሳዩ ሌዋውያኑን አመሰገነ። ለቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ሰባት ቀን የኅብረት መሥዋዕት አቅርበው ከበሉ በኋላ፥


የቀረበውን ገንዘብ ከግምጃ ቤት ያወጡ በነበሩበት ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ሒልቂያ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ፤


ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤተ መቅደሱ አግብተው በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ከኪሩቤል ክንፎች በታች በሚገኘው ስፍራ አኖሩት።


ሰሎሞን “የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ያለበት ስፍራ ሁሉ ቅዱስ ስለ ሆነ፥ ግብጻዊት ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤተ መንግሥት ውስጥ መኖር አይገባትም” በማለት የግብጽ ንጉሥ ልጅ የሆነችውን ሚስቱን ከዳዊት ከተማ አውጥቶ እርሱ ወዳሠራላት ወደ ሌላ መኖሪያ ቤት ተዘዋውራ እንድትኖር አደረገ።


ሙሴም ሌዋውያንን እንዲህ አለ፤ “ዛሬ ልጆቻችሁንና ወንድሞቻችሁን በመግደል እግዚአብሔርን የምታገለግሉ ካህናት ሆናችሁ ራሳችሁን ቀድሳችኋል፤ እግዚአብሔርም በረከቱን ሰጥቶአችኋል።”


ካህን የሠራዊት አምላክ መልእክተኛ ስለ ሆነና ሕዝብም ከእርሱ ዕውቀትን ስለሚፈልግ የካህን አንደበት ዕውቀትን ጠብቆ ማኖር አለበት።


የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።”


እኛ የምናስተምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ራሳችን ስለ ኢየሱስ የእናንተ አገልጋዮች መሆናችንን ነው እንጂ ስለ ራሳችንስ አንሰብክም።


ሥርዓትህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣን ያጥናሉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም በመሠዊያህ ላይ ያቀርባሉ።


跟着我们:

广告


广告